ለደቡብ እና ትግራይ ክልሎች የወባ መከላከያ አጎበሮች ሊሠራጩ ነው፡፡

May 26, 2020ፊውቸርድ ዜና
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከGlobal fund ጋር በመተባበር 2.8 ሚሊየን የወባ መከላከያ አጎበሮችን ሊያሠራጭ መሆኑን የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች ስርጭትና ተሽከርካሪ ስምሪት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው በቀለ ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡
አጎበሮቹ በደቡብ እና በትግራይ ክልሎች ለሚገኙ 72 ወረዳዎች እንደሚሠራጩ አቶ ሽፈራው አስታውቀው ስርጭቱ የሚካሄድባቸው ዞኖችም ሲዳማ፣ ከንባታ ጠንባሮ፣ ጉራጌ፣ ሃድያ፣ ከፋ፣ዳውሮ፣ ሸካ፣ ካንታ ልዩ ዞን፣ ማዕከላዊ፣ ሠሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ዞኖች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
ዳይሬክተሩ ኤጀንሲው ከ3 ዓመት በፊት ያሠራጨውን አጎበር የቅያሪ ስራ እያከናወነ መሆኑንና አንድ አጎበር ለ3 ዓመት ብቻ እንደሚያገለግል በቃለመጠይቁ ያስረዱ ሲሆን አጎበሮቹ 179 ሚሊየን ብር ዋጋ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡