በመድኃኒት ጥራት ላይ ለሚታዩ ችግሮች መፍትሔ እየተሰጠ ነው
January 17, 2020ፊውቸርድ ዜና
የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በመድኃኒት ጥራት ላይ ለሚነሡ ችግሮች የቅሬታ መቀበያ መንገዶችና የመፍትሔ አሰጣጥ አሠራሮች ተዘጋጅተው እየተሰራባቸው እንደሚገኝ የጥራት ቁጥጥርና ክትትል አስተባባሪ አቶ ታደሰ አየለ ተናግረዋል፡፡
አስተባባሪው ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት ቃለ ምልልስ እንዳስረዱት ከደንበኞች የሚነሱትን የመድኃኒት ጥራት ችግሮች ቅሬታ ለመቀበል ሦስት መንገዶች ተዘጋጅተው ቅሬታቸውን በመቀበል ላይ እንዳሉ ገልጸዋል፡፡
የቅሬታ መቀበያ መንገዶቹ 8772 ነጻ የስልክ ጥሪ መቀበያ መስመር፣ የኤጀንሲው ዌብ ሳይት ላይ የተዘጋጀ ፎርም እና ቅርንጫፎች ከደንበኞቻቸው የተቀበሉትን ቅሬታ ለዋናው መ/ቤት በደብዳቤ የሚልኩበት መንገድ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የተሰበሰበው ቅሬታ ላይ የተገለፀው መድኃኒት በተባለው መልክ ችግር አለበት ወይ የሚለውን ለማጣራት ምርቱን በአካል (በዐይን በማየት) Physical Inspection መጀመሪያ ይጣራል፣ በዓይን ታይቶ /Physical Inspection/ መለየት ካልተቻለ ለምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን በደብዳቤ በማሳወቅ እንደሚጣራ አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡