በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለሠራተኞቹ በነጥብ የስራ ምዘና /JEG/ዙሪያ ጥር 4/2012 ዓ.ም ኤሬንቴሽን ተሰጥቷል።

፨በነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ኦሬንቴሽን ፦
.ድልድሉ የተጠያቂነትና ግልፀኝነት መርህን የተከተለ መሆኑ
.ድልድሉ የሜሪት ስርዓቱን መሠረት ያደረገ
. ትክክለኛውን ሰራተኛ በትክክለኛ ቦታ ለማስቀመጥ
.ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ ለሚያሟሉ የአካል ጉዳተኞች:ሴቶች እና አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን ብሄረሠብ ተዋፅኦ ያካተተ
.የድልድል ውጤቱ ይፋ እስከሚሆን በሚስጥር መያዝ እንዳለበት
.በፐብሊክ ሰርቪስ ተመዝነው ደረጃ በወጣላቸው መደቦች ብቻ እንደሚደረግ
. የድልድል ውድድሩም ከከፍተኛ ወደ ዝቅተኛ መደቦች ሥራተኞች በግልፅ ማስታወቂያ ተጋብዘው እስከ ሁለት የስራ መደቦች ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ
. አንድ ሠራተኛ ለሚወዳደርበት የስራ መደብ ባለው ቅርበት መጠን ሙሉ በሙሉ አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ለድልድል እንደሚያዝ
.አስከ አንድ አመት የጎደለው እና ለስራ መደቡ የተቀመጠውን ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የሚያሟሉ ሌላ ሠራተኛ ከሌለ ሠራተኛውን መድቦ ማሠራት እንደሚቻል
.ሠራተኛች በውድድር ወቅት እኩል ከሆኑ በስራ አፈፃፀማቸው፣በትምህርት ዝግጅት አና በስራ ልምዳቸው በቅደም ተከተል እንደሚለዩ
፨በይይት ወቅት የተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች
.ጂኢጅው ማስተር የተማርነውን አላካተተም። መማርን አላበረታታም።
.ኤጀንሲው የመንግስት ባለበጀት መ/ቤት ባለመሆኑ ልዩ ስኬል ከተፈቀደላቸው ተቋማት ጋር መካተት ነበረብን።
.የስራ ልምድ፣ የትምህርት ዝግጅት እንድሁም አጫጭር ስልጠናዎች አያያዝ ቢብራራ
.አነስተኛ ቁጥር የብሄረሰብ ተዋፅኦ የተባለው እንደ ሀገር ነው ወይስ እንደ ኤጀንሲ
.ውጤት ተኮር በተደራጀና በትክክል መያዝ ነበረበት
.ምደባው ከሀላፊዎች ተፅእኖ የፀዳ እንድሆን
.በኦድት :በጸሀፊነት:በሹፌር ረዳትነት፣በድራጊስት እንድሁም በድፕሎማ እና ኮሚኒኬሽን የተገኙ የስራ ልምድ አያያዝ ቢገለፅ
.ለፖሊሲ እና ስትራቴጅ የተቀመጡ ነጥቦች ሽርፍራፊ ወይም ክፍልፍይ ነጥብ መስጠት እንደማይቻል
.የሀላፊነት የስራ መደቦች የሚባሉት የትኞቹ ናቸው የአመራርነት ክህሎት መለኪያውስ
. እንደኛ መ/ቤት ኘሳ የሚባሉትን አናውቃቸውም የደረጃ ተጠቃሚ ነን ወዘተ የሚሉ ሀሳቦች ቀርበዋል።
፨ በአለቱም ከፐብሊክ ሰርቪስ በተጋበዙት ባለሙያ ሰፊና ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ከተሰጡት ማብራሪያ በትቂቱ
.ፕሳ እና ደረጃ አቻ ግመታ የተሠጠ መሆኑን
.ለተነሱና ለሚነሱ የግልፀኝነት ሀሳቦች በደብዳቤ ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚቻ
.ሠራተኞች በተፈቀዱላቸው የስራ መደቦችና ደመወዝ ምርጫቸውን አስተካክለው መመደብ እንደሚገባቸወ
.በመወዳደሪያ መስፈርቶቹ መሠረት ተመዝኖ ከ 50%በታች ውጤት ያመጣ ሰራተኛ ሲገኝ ለአመለከተው መደብ እንደማይደለደል
.የመንግስት ተሿሚዎች ይህ የድልድል መመሪያ እንደማይመለከታቸው
.ለዳይሬክተርነት :ለስራ አስኪያጅ እንድሁም ም/ስራ አስኪያጅ የስራ መደቦች በመወዳደሪያ መስፈርቶቹ ከ100%የተገኘው ውጤት ወደ 80%ተቀይሮ ለቀሪው 20% የመ/ቤቱ የባላይ ሀላፊ የመወዳደሪያ መስፈርት አዘጋጅቶ ወጤት እንደሚሞላ
.በሀገር አቀፍ ደረጃ አብዛኛው የስራ መደቦች በመጀመሪያ ድግሪ የትምህርት ዝግጅት እንደተጠናቀቀ ሆኖም ግን ኤጀንሲው እነዚህ የስራ መደቦች በማስተር ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የትምህርት ዝግጅቶች ይሸፈኑልኝ ብሎ የፕሮጀክት ፅ/ቤቱን ጠይቆ ከተፈቀደ በኋላ የትምርት ዝግጅታቸውን ያሻሻሉ ሠራተኛች መወዳደር እንደሚችሉ
. ትምህርት ላይ ያሉ ሥራተኞች በትምህርት የቆዩበት የስራ ልምድ አይያዝም
.የስራ ልምድ አያያዝ የድልድል ኮሚቴ በይፍ ስራ መጀመሩ ለሠራተኞች ከተገለፀ እና እርክብክብ ከተደረገ በኋላ የይያዝልኝ ጥያቄ ማቅረብ እንደማይቻል
.የአነስተኛ ብሄረሰብ ተዋፅኦ እንደ መ/ቤት እንደሚመለከት
.የቀድሞ ኘሳ1እና 2 አሁን ተዋረድ 1፣ኘሳ3እና4 አሁን ተዋረድ 2፣ኘሳ5እና6 አሁን ተዋረድ 3 እንድሁም ኘሳ 7 እና 8 አሁን ተዋረድ 4 ላይ እንደሆኑ እና ድፕሎማ ያላቸው ሰራተኞች በተዋረድ አንድና ሁለት ላይ እንደሚወዳደሩ
.ውጤት ተኮር የሁለት ጊዜ አማካኝ የሚያዝ ሲሆን በተለያየ ምክንያት ያልተሞላ ከለ የአንድ ጊዜ እንደሚያዝ
.የፀሀፊነት የስራ ልምድ አያያዝ ቀደም ብሎ ጥቅምት 25/2007 በመጣው መመሪያ መሰረት እንደሚያዝ
.የድልድሉ አላማ አንድም ሠራተኛ ሳይፈናቀል ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛ ቦታ መድቦ ማሠራት እንደሆነ ተገልጿል።
supply chain of compassion!!!