በኤጀንሲው ከጀርመን መንግስት በድጋፍ የተገኘውን ኮቪድ -19 የክትባት መድኃኒት ርክክብ አካሄደ ፡፡
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከጀርመን መንግስት በድጋፍ የተገኘው የአስትራዜኒካ የኮቪድ-19 የክትባት መድኃኒት የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በተገኙበት መስከርም 7ቀን 2013 ዓ.ም ርክክቡ ተካሄዷል፡፡
በድጋፍ የተገኘው የክትባት መድኃኒት 271 ሺህ 200 ደዝ ሲሆን የጀርመን መንግስት ኮቫክስ (COVAX) በተባለ አለም አቀፍ ጥምረት አማካኝነት ለኢትዮጵያ መንግስት የተደረገ ድጋፍ ነው፡፡የጀርመን መንግስት በዓለም ላይ የተከሰተውን የኮቪድ -19 ወረርሽኝ በጋራ ለመዋጋት ተጨማሪ የክትባት መድኃኒት ለኢትዮጵያ መለገሱን የጀርመን በኢትዮጵያ አምባሳደር ሀይኮ ኒች ተናግረዋል፡፡
የክትባት መድኃኒቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ላለው የክትባት መረሃ ግብር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የተገለጸ ሲሆን 2.2 ቢሊየን ዩሮ ወጪ እንዳለው ተነግሯል ፡፡ከዚህ ቀደም ወደ 2 ሚሊየን ዶዝ የሚጠጋ የአስትራዜኒካ የተሰጠ መሆኑን ዶ/ር ሊያ አስታውሰው አሁንም በተጨማሪ ሁለተኛውን ክትባት ያልወሰዱ ሰዎችን ክትባቱን ለመስጠት እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡በሀገር አቀፍ ደረጃ ሶስት አይነት የክትባት መድኃኒቶች እየተሰጡ የሚገኙ ሲሆን ይህም ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን፣ ሳይኖ ፋርምና አስትራዜኒካ በአጠቃላይ ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ የክትባት ዶዝ መሰጠታቸውን ሚንስቴሯ አብራርተዋል፡፡
እንዲሁም ሁለተኛውን ዙር ክትባት ጨምሮ 2.4 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች መከተባቸውን ገልጸዋል፡፡አሁን ላይ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ እየጨመረ በመምጣቱ በሽታውን ለመከላከል ዋነኛ መከላከያው መንገድ ክትባቱን መውሰድ በመሆኑ ህብረተሰቡ ይህን በመረዳት ክትባቱ መከተብ እንዳለበት ዶ/ር ሊያ አሳስበዋል ፡፡
በዕለቱ የጀርመን አምባሳደር ሀይኮ ኒች፣የUNICEF አምባሳደር ሚካኤል ሰርቫንድ ፣የኢፌዴር የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር እና የኤጀንሲው ዳይሬክተሮች በተገኙበት ርክክቡ ተካሄዷል፡፡