“አቀርባለሁ፤ አሻሽላለሁ፤ እጠየቃለሁ!”
።።።።።።።።።
የአገልግሎቱ ሀዋሣ ቅርንጫፍ ለነገ የተሻለ የአቅርቦት ስርዓት እንዲፈጠርና መሠረትን ለመጣል” ውጤትን በማጠናከር ተግዳሮትን ማረም” በሚል መሪ ቃል ተቋማዊ ሠነድ በማዘጋጀት ከግንቦት 8_10/2017 ዓ.ም. ለተከታታይ 3 ቀናት ከአጠቃላይ ሠራተኞቹ ጋር በመወያየት ላይ ይገኛል።
በውይይቱ የአገልግሎቱን ታሪካዊ አመጣጥ፤ የተቋሙ የለውጥ ጉዞዎች፤ በአቅርቦቱ ዙሪያ ያጋጠሙ ፈተናዎች፤ የስራ ከባቢ ምቹነት፤ የመሠረተ ልማት ስራዎች፤ የቁጥጥር ስራ፤ የክምችትና ስርጭት መሠረተ ልማት የማጠናከር ስራዎች፤ የዲጂታላይዜሽን ጉዞ እንዲሁም አገልግሎቱ ከሲቪል ሠርቪስ ወደ ራስ ገዝ ተቋም ግንባታ የተደረጉ አጠቃላይ የአገልግሎቱ ጉዞዎች ተዳሠዋል።
በተጨማሪም የሠራተኛው ሁኔታዎች፣ በለውጥ ጉዞ ውስጥ የተስተዋሉ ያልተሻገርናቸው ተግዳሮቶች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ምን መምሰል እንዳለባቸው ሰፊ ውይይት በመደረግ ላይ ነው።
አገልግሎቱ በማይበገር ስርዓት ግንባታ ውስጥ ቁልፍ ድርሻ ያለው በመሆኑ አጠቃላይ ሰራተኛው በአገልጋይነት መንፈስ ተቃኝቶ በብስለት መምራት እና ማስተባበር ከተቻለ ዘላቂና ቀጣይነት ያለው የመድኃኒት አቅርቦትን ማሣለጥ እንደሚቻልና የማህበረሰቡንም ጥያቄ መመለስ እንደሚቻል ተገልጿል።
ይህ ውይይት በተመሣሣይ በድሬዳዋ፣ በጅማ ፣ በመቀሌ እና በሁሉም ቅርንጫፎቻችን በመካሄድ ላይ ይገኛል።
#ማገልገል ክብር ነው!
