አጀንሲው በግዥ ያላስገባቸው ማሽኖች የመመርመሪያ ግብአት አለመገኘት ችግር እያስከተሉ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በሀገር ውስጥ 25 የሚሆኑ የላቦራቶሪ ኬሚስትሪ ማሽኖች እንደሚገኙ እና ከ እነዚህ ውስጥ በኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በኩል የገቡት ከ 6 እንደማይበልጡ የ ኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ሎኮ አብርሀም ተናግረዋል፡፡
የመመርመሪያ ግብአት/ Reagent/ አለመገኘት ችግር አጋጥሞናል የሚል ጥያቄ ከጤና ተቋማት ሲመጣ የማኛውቃቸው የ19 ማሽኖችም ጥያቄ አብሮ ይመጣል ብለዋል፡፡
ማሽኖቹ ከተለያዩ ሀገሮች በእርዳታ ለሆስፒታሎች የሚመጡ ከመሆናቸው ባሻገር የመመርመሪያ ግብአት በቀላሉ ገበያ ላይ ካለማገኘታችን እና ለአንድ ማሽን አንድ ግብዓት የሚጠቀሙ ዝግ ስርዓት/close system/ ያላቸው በመሆኑ የተከሰተ እጥረት ነው ብለዋል፡፡
የሀገራችንን የላቦራቶሪ ፕላት ፎርም ለማስታዳደር በጣም አስቸጋሪ በመሆኑ ሌሎች አገራት የሚሰሩበትን መንገድ መከትል ግድ ይለናል ብለዋል፡፡
ይህን ችግር በመረዳታችን ከባለፈው አመት ጀምሮ አዲስ የግዥ ስርዓት ወይም በ”ፕሌስመንት “ጨረታን አሰራር በመከተል ማሽኖችን በነጻ በማግኘት የመመርመሪያ ግብዓት / Reagent /በቀጣይነት በገባነው በውለታ መሰረት የምንገዛበትን አሰራር እየተገበርን ነው ብለዋል፡፡
ስለሆነም አሉ ዶ/ር ሎኮ ማሽኖቹን ያሰራጨንባቸውን ተቋማት ስለሚታወቁ የመመርመርያ ግብአት ለማድረስ አያስቸግርም በተመሳሳይ አቅርቦቱ እንዳይቆራረጡ ከአቅራቢዎች ጋር በውለታው መሰረት እንዲቀርብ ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡
እንደ ዋና ዳሬክተሩ ገለጻ እስከ 2012 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ በ 289 ሆስፒታሎች የሄማቶሎጅ እና የኬሚስትሪ ማሽኖች ከእነ ግብአቱ እንዲደርሳቸው እንሰራለን ብለዋል፡፡
በቀጣይም ከፍተኛ ታካሚ የሚያሥተናግዱ ጤና ተቋማትን በመለየት በመላ ሀገሪቱ ተደራሽ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
Supply chain of
compassion!!!!