አገልግሎቱ የመጨረሻዉን ዙር የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት (ERP)ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ገለፀ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በተለያዩ ሞጅሎች ላይ ለሰራተኞች ሲሰጥ የነበረዉን ስልጠና ለማጠናቀቅ የመጨረሻዉን ዙር ስልጠና በአዳማ እና በሀዋሳ ከተማ እየሰጠ እንደሚገኝ የኢ.አር.ፒ ፕሮጀክት የለውጥ ስራ አመራር ባለሙያ ወ/ሮ አድና በሬ ተናግረዋል፡፡
P2P ፣ In2Rep ፣ H2R ፣ EHS ፣ S2S ፣ I2R ሞጅሎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉን ስልጠና ባለፉት ሳምንታት ማጠናቀቁን እና EWM ፣ TM ፣ PL2Pr ፣ O2C እና F2R ሞጅሎች ላይ የመጨረሻዉን ዙር ስልጠና ከዋናዉ መ/ቤት እና ከቅርንጫፎች ለተወጣጡ ባለሙያዎች በተያዘዉ ሳምንት እየሰጠ እንደሚገኝ ወ/ሮ አድና ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡
ሰልጣኞች በጥሩ ስነ -ምግባር እና ተነሳሽነት እየተሳተፉ እንደሚገኙ የሲስተሙ አሰልጣኞ የተናገሩ ሲሆን ፤ ሲስተሙ በሚመራዉ መንገድ እያንዳንዱን ቅደምተከተል ተከትለዉ ለመስራት እና ሌሎችንም ለማብቃት በከፍተኛ ትጋት እየሰለጠኑ መሆናቸዉን ሰልጣኞች ተናግረዋል፡፡
ሲስተሙ ከባድ የሚመስለዉን ስራ በጣም በቀላሉ በመከዉን የአቅርቦት ጥራትን በማረጋገጥ አገልግሎቱ በአለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚያስችል በመሆኑ ሁሉም ሰራተኞች ኃላፊነታቸዉን በቁርጠኝነት መወጣት እንደሚገባቸዉ የO2C ሞጅል አሰልጣኝ አቶ መሰለ ብርሀኑ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ