አገልግሎቱ የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምን ገመገመ።
October 12, 2023Magazine
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የ2015 ዓ.ም በጀት አመት የስራ አፈፃፀሙን ከመስከረም 22-24/2016 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ ገመገመ።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ የመክፈቻ ንግግር እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በግምገማው ቁልፍ የስራ ሂደቶች አፈፃፀም ከ12ቱ ስትራቴጅክ ግቦች አንፃር፣ የህክምና ግብዓቶች በማዕከልና በቅርንጫፎቻችን የመገኘት ምጣኔና ስርጭት፣ የERP ትግበራ አሁን ያለበት ደረጃ በዝርዝር ቀርቧል፡፡
የፋይናንስ አጠቃቀም፣ የመድኃኒቶችን ብክነት ለመቀነስ የተሠሩ ስራዎች፣ ዓመታዊ፣ የሩብ አመት እንዲሁም እለታዊ የግብዓት ቆጠራ ካለው ፋይዳ አኳያ የተሠሩ እንዲሁም በቀጣይ ምን መሰራት እንዳለበት በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡
በመጨረሻም ባሳለፍነው የበጀት አመት የነበረንን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ዝርዝር የቀረበ ሲሆን የበለጠ የተሻለ አቅርቦት ለማምጣት የጋራ የድርጊት መርሃ ግብር በማዘጋጀት ግምገማው ተጠናቋል፡፡
በግምገማው የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፣ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ የቅርንጫፍ ስራ-አስኪያጆች እና የስራ ሂደት ቡድን መሪዎች ተሣትፈዋል፡፡
#ማገልገል ክብር ነው