አገልግሎቱ የ6 ወር እቅድ ክንዉኑን በመገምገም ላይ ይገኛል

February 24, 2025Magazine
አገልግሎቱ የ6 ወር አፈፃፀሙን እየገመገመ ሲሆን ፤ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ዳይሬክተሮች ፣ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች እንዲሁም ከኢ.አር.ፒ ፕሮጀክት ቢሮ በአዳማ ከተማ በመገኘት ክንዉናቸዉን በመገምገም ላይ ይገኛሉ።
የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ስርአት (ERP) አፈፃፀምና የግማሽ አመት የዉስጥ ኦዲት ክንዉን ዙሪያም ዉይይት እየተካሄደ ይገኛል።
አገልግሎቱ በጤና ፕሮግራም ደግሞ ከ17ቢሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ግብአቶችን ተቋሙ ማሰራጨት መቻሉን የገለፁት የእቅድ ዝግጅት ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ አበበ የግብአት መገኘት ምጣኔዉ 88.3% መድረሱንና ተቋማዊ እቅድ አፈፃፀሙም 79.3 ከመቶ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በ6 ወራት ዉስጥ የመድኃኒት ፈንድ አዋጅ ቁጥር 1354/17 መፅደቁ ፤ ተቋሙ ወረቀት አልባ የመረጃ ልዉዉጥ አሰራር (eDMS) መዘርጋት መቻሉን ፤ በየመጋዘኑ የካይዘን ትግበራ መስፋፋቱ ፤ በቀዝቃዛ ሠንሰለት እና ለደረቅ ጭነት አገልግሎት የሚውሉ የህክምና የግብአቶች ማሰራጫ ተሽከርካሪዎችን መጨመር እንደተቻለ አቶ ወርቅነህ አበበ ገልፀዋል።
#ማገልገል ክብር ነዉ
ዘጋቢ አማኑኤል ወርቃየሁ