ኤጀንሲው በቻይና መንግስት በእርዳታ የተሰጠውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ የሙቀት መጠን መለኪያ (ኢንፍራሬድን) ጨምሮ ሌሎች የህክምና ግብዓቶችን ማሰራጨት ጀመረ፡፡
==============================================
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በቻይና መንግስት በእርዳታ የተሰጠውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ የህክምና ግብዓቶችን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ የሙቀት መጠን መለኪያ (ኢንፍራሬድን) ጨምሮ ሌሎች የህክምና ግብዓቶች ከ መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለክልሎች እና ለከተማ አስተዳደሮች ማሰራጨት መጀመሩን የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች የክምችትና ስርጭት ዳይሬተር አቶ እንዳልካቸው መኮነን ገለጹ፡፡
እየተሰራጩ ያሉ የህክምና ግብዓቶች ቫይረሱን ለመለየት የሚረዱ የሙቀት መጠን መለኪያ Infrared thermometer)፣ የፊት መሸፈኛ ጭምብል (protective face mask for medical use)፣ የፊት መሸፈኛ ፕላስቲክ (Medical Protective Goggles)፣ የህክምና ባለሙያዎች የሚለብሷቸው መከላከያ ልብሶች (Disposable Protective Clothing) መሆናቸውን አቶ እንዳልካቸው ገልጸዋል፡፡
እነዚህ ለኮቪድ – 19 ኮሮና ቫይረስ ለመለየትና ለመከላከል የሚውሉ የህክምና ግብዓቶችን ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ላቋቋሟቸው የህክምና ለይቶ ማቆያ ተቋማት የሚሰራጭ ሲሆን በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲውት በሰጠው የስርጭት ክፍፍል መሰረት እየተሰራጨ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም በቻይና መንግስት ለተደረገልን ድጋፉ የኢትዮጵያ መንግስትን እና ኤጀንሲው በመወከል ምስጋና አቅርበዋል፡፡