ኤጀንሲው ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎችን ለማከም የሚውሉ መድኃኒቶችና ግብዓቶች አሰራጨ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በ2012 በጀት ዓመት ከ121 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ማከም የሚያስችል የሀሩራማ በሽታ መድኃኒቶችን ማሰራጨቱን የአቅርቦት ሰንሰለት አማካሪ የሆኑት አቶ ዳንኤል ተፈሪ ነሐሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ገለጹ፡፡
ኤጀንሲው ለአምስት ዓይነት ትኩረት የሚሹ የሀሩራማ በሽታዎች መድኃኒቶች እደላ ያከናወነ ሲሆን 10.2 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ እንዳለቸውና በ 2 ዙር መካሄዱን ባለሞያው አብራርተዋል፡፡
ከተሠራጩት መድኃኒቶች መካከል የትራኮማ፣ የኦንኮሰርኪያሲስ፣ የብልሀርዚ፣የአንጀት ጥገኛ ትላትል፣ የዝሆኔ፣የካላዛር መድኃኒቶችና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ግብዓቶች የተሰራጩ ሲሆን 121 ሚሊዮን 562 ሺህ 950 ሰዎች ማከም እንደሚያስችል አቶ ዳንኤል ገልፀዋል፡፡
ስርጭቱም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ለድሬደዋ ከተማ አስተዳደር፣ለአማራ፣ ለአፋር፣ ለኦሮሚያ፣ ለትግራይ፣ ለሶማሊያ፣ ለሐረር፣ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ለጋምቤላና ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች መሆኑን ዓመታዊ ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡
ሂሩት ኃይሉ