ኤጀንሲው ከተባበሩት መንግስታት (UNOPs) ጋር የክትባት መጓጓዣ ተሽከርካሪዎችና ለሎች ተያያዠ መገልገያዎች የግዥ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡==========================

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከተባበሩት መንግስታትThe United Nations Office for Project Services/ UNOPs / ጋር የግዥ መግባቢያ ስምምነት የካቲት 02/2013 ዓ.ም ተፈራረመ፡፡
በግዥ የሚቀርቡት የማቀዝቀዣ ክፍል የተገጠመላቸው የተለያዩ ተሽከርካሪዎች /different types of cold chain equipment , vehicles, CCE, MHE, / እና ሌሎችም ግብአቶች ግዦች ታክለው የክትባት አቅርቦት ሰንሰለት አያያዝን ለማጠናከር የሚውሉ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
በኤጀንሲው በኩል ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር አብዱልቃድር ጋልጋሎ እና የUNOPs መልቲ ካንትሪ /ሱዳን፡ጅቡቲ እና ኢትዮጵያ / እና በአፍሪካ ህብረት ተወካይ የሆኑት የድርጅቱ ዳይሬክተር ወ/ሮ ወርቅነሽ መኮነን የመግባቢያ ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡በስምምነቱ መሰረት ግዥው በአጭር ጊዜ ዉሰጥ ተጠናቆ ለተፈለገው አላማ እንዲውል እምነታቸው መሆኑን ዶ/ር አብዱልቃድር ጋልጋሎ ገልጸዋል፡፡
እጀንሲው የተለያዩ ግብአቶችን በእኛ በኩል እንዲገዙለት በጠየቀው መሰረት አለም አቀፍ የግዥ ስርአትን ተከትለን ከተለያዩ ካምፓኒዎች ጋር በአለም አቀፍ ደረጃ ባለን ስምምነት መሰረት የተፈጠነ እና የተሳለጠ ግዥ እንደሚፈጸም የUNOPs በኩል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ወርቅነሽ መኮነን ተናግረዋል።
ለግዥው 6.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተመደበ ሲሆን ፣ የበጀት ድጋፋ የተገኘው በአለም አቀፍ ደረጃ የክትባት አቅርቦትን ለማሻሻል የሚሰራ/ Global Alliance for Vaccine initiative /የተባለው ግብረ ስናይ ድርጅት ነው ።