ኤጀንሲው ከአገር ውስጥ አቅራቢዎች ገዝቶ ለጤና ተቋማት ለማቅረብ ካወጣው 109 የመድሀኒት አይነቶች እሰከ የካቲት ወር መጨረሻ በአቅራቢወች ማቅረብ የቻሉት 25 አይነቱን ብቻ በመሆኑ በአቅርቦት ላይ ችግር ፈጥሮበኛል ሲል ገለፀ።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ መጋቢት 8 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባካሄደው የውይይት መድረክ ከሀገር ውስጥ የ መድኃኒት አምራቾችና አቅራቢዎች በዋናነት የሀገር ዉሰጥ የመድኃኒት ፈላጓታችን ለሟሟላት እየሰሩ ቢሆንም በአለማችንም ሆነ በሀገራችን በተከሰተው ኮሮና ቫይረስ አፈጻጸማቸው በጣም ዝቅተኛ ነው። በ2012 አፈጻጸማቸው 20% ሲሆን በያዝነው በጀት አመት እስከ የካቲት ወር ድረስ በሀገር ውስጥ የመድሀኒት አምራቾችና አቅራቢወች አቅአፈፃፀማቸው 22% ብቻ ነው። ይህም በመሆኑ ኤጀንሲው ከአገር ውስጥ አቅራቢዎች ገዝቶ ለጤና ተቋማት ለማቅረብ ካወጣው 109 የመድኃኒት አይነቶች ውስጥ እሰከ የካቲት ወር መጨረሻ የሀገር ውስጥ አቅራቢወች ማቅረብ የቻሉት 25 አይነቱን ብቻ በመሆኑ በ አቅርቦቱ ላይ ችግር አንደሆነበት በነበረው የምክክር መድረክ ወቅት በአፅንኦት ተገልጿል።በነበረው ውይይትም አቅራቢዎቹ በኩል መድኃኒት ለማምረት የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎችን ከሃገር ውጭ ለማምጣት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ፣ የጥሬ እቃ ዋጋ መጨመር ፈተና አንደሆነባቸው አና ለሎች ምክንያቶችም የተነሱ ስሆን እነዚህን ችግሮች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመቅረፍ እንደሚሞክሩ አብራርተዋል።በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ጋልጋሎ የሀገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾችና አቅራቢዎች ያለባቸሁን ችግሮች በፍጥነት ቀርፍችሁ የሚጠበቅባችሁን አቅርቦት እንዲታሻሽሉና የሰውን ህይወት የማዳን ሀገራዊ ተልእኳችሁን በብቃት እንድወጡ በማለት ገልፀዋል ።
ሂሩት ኃይሉ