ኤጀንሲው የሚዝልስ ክትባት መድኃኒት ማሠራጨቱን ገለፀ፡፡
November 19, 2019ፊውቸርድ ዜና
ኤጀንሲው በሐረር ከተማ ለተከሠተው የኩፍኝ ወረርሽኝ የሚዝልስ /ኩፍኝ/ ክትባት መድኃኒት ማሠራጨቱን የክትባት ፕሮግራም መድኃኒት ክትትል ባለሞያ ወ/ት ናዲያ ሲራጅ ለዝግጅት ክፍሉ አስታወቁ፡፡
ወረርሽኙ በተከሠተባቸው ወረዳዎች የሚገኙ ከ5 ዓመት በታች ላሉ 15 ሺህ 298 ሕፃናት የሚውል የክትባት መድኃኒት ለማሠራጨት ኤጀንሲው ዝግጅቱን አጠናቋል ሲሉ ባለሙያዋ አብራርተዋል፡፡
ወረርሽኙ በ3 ወረዳዎች ላይ መከሠቱንና ወረዳዎቹም ሶፊ፣ ይረር እና ድሬ ታየር መሆናቸውን ገልፀው ኤጀንሲው 16 ሺህ 981 የሚዝልስ ክትባት መድኃኒቶችን እንዳሠራጨ እንደ ባለሙያዋ ተናግረዋል፡፡
በጸሎት የማነ