የህክምና ግብአትን ቀጥታ ወደ ጤና ተቋማት(Last Mile delivery) ለማድረስ የሚያግዙ 62 ተሽከርካሪዎች የርክክብ ስነ ስርአት ተካሄደ

የህክምና ግብአቶችን የመጨረሻው ጠቃሚ ጋር ለማድረስ የሚውሉ በመንግስትና ለጋሽ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ የተገዙ 62 ተሽከርካሪዎች የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፣ የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የለጋሽና አጋር ድርጅት ተወካዬች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለአገልግሎቱ 19 ቅርንጫፎች የርክክብ ስነስርአት በሚሊኒየም አዳራሽ ተከናውኗል።
የቀጥታ ስርጭት ተደራሽነት ለማስፋፋት አለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶችን በማስተባበር ከጋቪ ፣ ከአፍሪካ ሲዲሲ እና ከግሎባል ፈንድ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ 6ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገባቸው ተሽከርካሪዎች ለማህበረሰቡ ፈጣን ፣ ቀልጣፋ እና ፍትሀዊ አገልግሎት ለመስጠት ያስችሉናል ሲሉ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።
ተሽከርካሪዎች የዘመኑን ቴክኖሎጂ የዋጁ እና የመድኃኒቱን ልዩ ባህሪ ባገናዘበ መልኩ ተጠቃሚው ጋር ማድረስ የሚያስችሉ በመሆኑ የቀዝቃዛ ሰንሰለት ስርአቱን ለማጎልበት ፣ የስርጭት ውጤታማነት ለማሻሻል እና ወጥ የሆነ የመድኃኒት አቅርቦትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ አንስተዋል።በሌላ በኩል እነዚህን ተሽከርካሪዎች ገዝቶ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ሂድት ውስጥ ድርሻ ለነበራችሁ አካላት ከፍተኛ ምስጋና አቅርበእወዳልሁ
ድጋፉ በከተማና በገጠር መከካል ያለውን የህክምና ግብዐት አቅርቦት የተመጣጠነ በማድረግ ህይወት አድን መድኃኒቶችና ክትባቶች በሚፈለጉበት ቦታና ጊዜ አቅርቦት እንደሚኖር በማመን የተለገሰ መሆኑን በምስራቅ አፍሪካ የአፍሪካ ሲዲሲ ዳይሬክተር ዶ/ር ማዘንጊያ ሉሲ ተናግረው ፤ በቀጣይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ዘላቂ የሆነ ድጋፍ የማድረግ እቅድ እንዳላቸው ገልፀዋል ።
ማገልገል ክብር ነው!
ሰላም ይደግ