የሲስተም ስልጠናዉ በጥሩ ሁኔታ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገለፀ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከመጋቢት 2/2016 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ሞጅሎች ላይ የሲስተም ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል ፤ በዚህም P2P 3ተኛ ዙር F2R ፣ EWM ፣ እና S2S 2ተኛ ዙር እንዲሁም H2R ሞጅል የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በአዳማ እና በሀዋሳ ከተማ መሰጠቱን ቀጥሏል፡፡
የሲስተም ስልጠናዉ በሚፈለገዉ አግባብ እና በቀላሉ እየተሰጠ እንደሚገኝ የንብረት አስተዳደር ወይም የ S2S ሞጅል አሰልጣኝ አቶ አየልኝ ጥጋቡ ተናግረዋል ፤ ሲስተሙ ከአገልግሎቱ አልፎ የጤና ዘርፉን አንድ እርከን የሚያሻግር ከመሆኑ አኳያ ሰልጣኞች በትልቅ ተነሳሽነት እየወሰዱ እንደሚገኙ የሲስተሙ የሰው ሀብት አስተዳደር ወይም H2R ሞጅል አሰልጣኝ ወ/ሪት ፋሲካ ለገሰ ገልፀዋል፡፡
የመዉጫ ፈተና የወሰዱ ሰልጣኞች ከ60% በላይ ዉጤት በማምጣት ሁሉም በሚባል ደረጃ ጥሩ ዉጤት ማስመዝገባቸዉን የEWM ሞጅል አሰልጣኝ አቶ ብላታ ሸኮ አንስተዉ ፤ስልጠናዉ በቀላል አቀራረብ እና ከዚህ በፊት ከተሰጡ ስልጠናዎች በተሻለ መልኩ እየተሰጣቸዉ መሆኑን በስልጠናዉ ተሳታፊ የሆነዉ የሀዋሳ ቅርንጫፍ የመጋዘን አያያዝ እና ክምችት አስተዳደር ባለሙያ አቶ ዳዊት ኤልያስ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናዉ ሀላፊነት በተሞላበት መልኩ እየተሰጠ መሆኑን ገልጸው ከዚህ አኳያ ሰልጠኞች ያገኙትን እዉቀት የበለጠ በማደበር በተሻለ ብቃት ከስሮቻቸዉ ያሉ ሰራተኞችን ማብቃት እንደሚገባቸዉ አቶ ብላታ ገልፀዋል፡፡
#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ
