የባህርዳር ቅርጫፍ አመታዊ ምርጥ የባለ ድርሻ አካል ተብሎ ተሸለመ፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት #የባህርዳር ቅርጫፍ አመታዊ ምርጥ #የባለ ድርሻ አካል ተብሎ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመድኃኒት እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተሸለመ፡፡በኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ በገበያ የዋጋ ንረት ሳቢያ በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ፈተና በሆነበት ወቅት ጥበበ ግዮን #ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል (TGSH)የመድኃኒት ፍላጎቶችን በከፊል ለማሟላት ባደረገው አስደናቂ ጥረት የኢትዮጵያ #መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እንደተመረጠ ከዩኒቨርስቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ #በዩንቨርስቲው ማህበራዊ የትስስር ገጽ ላይ እንደተገጸው ባለፈው አመት ተለዋዋጭነት እና ሌሎች ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች እያሉ የመሰረታዊ የመድኃኒቶች አቅርቦት መጠንን 75% ለ ሆስፒታሉ (TGSH ) ቅርንጫፉ በማቅረብ ቁልፍ ሚና እንተጫወተ ተገልጿል፡፡ ምንም እንኳን ዓለም አቀፋዊ ቀውስ በጤናው ዘርፍ እና በፋርማሲ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ቢሆንም የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የባህር ዳር ቅርንጫፍ ምርጥ የዓመቱ #ባለድርሻ አካል እውቅና ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ማግገኘቱ በቀጣይ አስር አመታት የደንበኞችን እርካታ ለማሰደግ ቁልፍ ተግባር ተደርጎ በመድኃኒት አቅራቢ አግልሎት በኩል የተያዘው እቅድ አካል መሆኑን የገለጹልን የባህርዳር ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ እና የሰሜን ምእራብ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አምሳሉ ጫኔ ናቸው፡፡እንደ አቶ አምሳሉ ገለጻ ቅርጫፉ #ከሆስፒታሎች ጋር በቅርበት እና በትብብር በመስራት መረጃዎችን በመለዋወጥ በእጅ ላይ ያሉም ሆነ አዲስ የገቡ መድኃኒቶችን በተመለከተ የሪፖርቶች ልውውጥ በየጊዜው ይደረጋል ብለዋል፡፡የጤና ተቋማት ተገቢ በጀት መድበው ፍላጎታቸውን መሰረት ያደረገ የህክምና ግብአቶችን ማቅረብ እንደሚገባ ገልጸው በበጀት እጥረት ምክንያት የሚፈጠር ክፈተትን ለመሙላት እንዲቻል ታስቦ ተቀናጅቶ እየተሰራ እንዳለ አቶ አምሳሉ ገልፀዋል፡፡
አወል ሀሰን