የነጌሌ ቦረና ቅርንጫፍ በመድኃኒት አቅርቦት መጠየቂያ ፎርም (RRF) ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄዴ።

September 22, 2021Featured News
በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የአርባ ምንጭና የነጌሌ ቦረና ቅርንጫፎች በስራቸው ከሚገኙ የዞን ጤና መምሪያ ሎጅስቲክ ባለሞያዎች ጋር በመድኃኒት አቅርቦት መጠየቂያ ላይ መስከረም 10 ቀን 2014ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ውይይት አካሄደዋል።RRF የጤና ተቋማት የመድኃኒት ፍላጎታቸውን ከኤጀንሲው የሚጠይቁበት ቅፅ ሲሆን የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማሳለጥና ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እነደሚኖረው የነጌሌ ቦረና ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድወሰን ማዘንጊያ ገልፀዋል።የውይይቱ ዓላማ ከዞኑ የሎጅስቲክ ባለሞያዎች ጋር የበለጠ ተቀራርቦና ተናቦ ለመስራት እንደሆነ ስራ አስኪያጁ አክለዋል።በውይይቱ ላይ የሱማሌ፣የደቡብና የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ተወካዮች፣ የሎጅስቲክ ባለሞያዎች፣የክልሎቹ የጤና መምሪያ ሀላፊዎች፣ የአርባ ምንጭና የነጌሌ ቦረና ስራ አስኪያጆች ተሳትፈዋል።