የአዳማ ቆጠራ በሁለት ቀናት ውስጥ ተጠናቀቀ
July 24, 2019ፊውቸርድ ዜና
የመድኃኒትና የህክምና ግብዓቶችን ቆጥሮ ለማጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ ፈጅቶብናል ሲሉ የአዳማ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ንጉሤ ተናገሩ፡፡
ሐምሌ 16 ቀን ከዝግጅት ክፍሉ ጋር ባደረጉት ቆይታ ቆጠራውን ለማጠናቀቅ በቅድመ ቆጠራ የተሠራው የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራና የልህቀት ማዕከል ሥራ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል፡፡
በቆጠራው በተገኘው ውጤት 956 ሚሊየን ብር የጤና ፕሮግራም መድኃኒቶችና 235 ሚሊየን ብር የተገላባጭ ፈንድ መድኃኒቶች ማሰራጨቱን አቶ ሰለሞን አሳውቀዋል፡፡
በቀጣይ የቀን ተቀን ቆጠራውን ለማወቅና ለማመሳከር የሰው ሀብት መመደቡን ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም በቆጠራው የኮምፒውተር ሲስተሙና በአካል የሚደረገው ቆጠራ 98 በመቶ መናበቡን ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ለመጋዘን ሥራ የሚሰጠው ግምት ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩና የኤጀንሲው ኃላፊዎች ለቆጠራ የሰጡት ትኩረት ይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል፡፡
ከሐምሌ 4 ቀን ጀምሮ አዳማ ቅርንጫፍ ወደ አገልግሎት መግባቱን ከተደረገው የስልክ ቆይታ መረዳት ተችሏል፡፡