የአገልግሎቱ አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ በቀጥታ ስርጭት (Last Mile Delivery) የሚሰጣቸውን የጤና ተቋማት ማሳደጉን አስታወቀ፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ለመንግስት የጤና ተቋማት የሚሰጠውን ቀጥታ ስርጭት አገልግሎት (Last Mile Delivery) ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል ፤ በዚህም አርባምንጭ ቅርንጫፍ ከ43% ወደ 67.5% በጥቅሉ 259 የጤና ተቋማትን የጤና ፕሮግራም ግብአቶችን በቀጥታ ያደርሳል።
በ2015 ዓ.ም ጥቅምት ወር ላይ ለክትባት መድኃኒቶች በቀጥታ የሚደርስባቸው የጤና ተቋማት ብዛት 41 የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ ወደ 101 ማሳደግ መቻሉን የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ አንድነት አሰፋ ገልፀዋል፡፡
የቀጥታ ስርጭት አገልግሎቱ እንዲሻሻል ከተሰሩ ስራዎች መካከል በቀጥታ የሚደርስባቸው ሁሉም የጤና ተቋማት በአግባቡ ሪፖርት የማዘጋጀት አቅምን በስልጠና በማገዝ ሪፖርት እንዲልኩና በዛ መሰረት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ አንዱ ሲሆን ፤ ሌላኛው የሞዴል 19 አሰባሰብን ማሻሻል በመሆኑ የሞዴል 19 ምንነትን ግንዛቤ መፍጠር እና አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን በመውሰድ በ2015 ዓ.ም መጨረሻ ላይ 99.6 % መድረሱን ስራ አስኪያጁ ተናግረው፤ በቀጣይም የሚሰበሰቡ ሞዴል 19 ጥራት ያላቸው እንዲሆኑ ትኩረት እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
ማገልገል ክብር ነው !!
ማኅሌት አበራ
