የአገልግሎት ተቋሙ ድርቅ ለተከሰተባቸው ዞኖች ከ15 ሚሊየን በላይ ዋጋ ያላቸው ግብዓቶችን አሰራጨ፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ድርቅ ለተከሰተባቸው ዞኖች ከ15 ሚሊየን በላይ ዋጋ ያላቸው ግብዓቶችን ማሰራጨቱን የመደበኛ ፕሮግራም ክምችት ባለሙያ አቶ አገኘሁ ናደው የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም አስታወቁ፡፡ የተሰራጩት ግብዓቶችም በዞኖች ከተከሰተው ድርቅ ጋር ተያይዞ ለሚከሰቱ የተለያዩ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣተር የሚያስችሉ የተለያዩ መድኃኒቶች ፣የህፃናት አልሚ ምግቦች እንዲሁም ውሃ ወለድ በሽታዎችን ማከሚያ መድኃኒቶች መሆናቸውን ባለሙያው አብራርተዋል፡፡ ከተሰራጩት ግብዓቶች መካከል Artemether + Lumefanthrine – 20mg + 120mg (6×4) – Tablet , Primaquine Phosphate – 7.5mg base – Tablet, Serology -Malaria, Rapid Diagnostic Test (MRDT), PF&PV Cassette – , Sulphamethoxazole + Trimethoprim – (800 mg + 160 mg) – Tablet , Adhesive Plaster Zinc Oxide -12.5cmx10m, Plumpy Nut, Ready to Use Theurapeutic Food (RUTF) – – Paste ለአብነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ስርጭቱም በአዳማ፣ በጅጅጋ፣ በነጌሌ ቦረና፣ በድሬደዋና በአርባ ምንጭ ቅርንጫፎች አማካኝነት ለሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ፣ ለምስራቅ ሀረርጌ፣ ለደቡብ ኦሞ ፣ ለምስራቅ ባሌ ፣ ለቦረና ለዳዋ ዞኖች የተካሄደ ሲሆን 15 ሚሊየን 619 ሺህ 65 ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡
ሂሩት ኃይሉ