የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አገልግሎቱን ጎበኙ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የጤና ጉዳይ ማህበራዊ እሴቶች እና ባህል ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአመት ሁለት ጊዜ የጤና ሴክተሩን የሚከታተልና የሚደግፍ ሲሆን፤ የምክር ቤት አባላቱ የአገልግሎቱን ክንዉን ጎብኝተዋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ለምክር ቤት አባላቱ ተቋሙ እያከናወነ ያለዉን ሪፎርም ያስገነዘቡ ሲሆን የመድኃኒት አያያዝና ግዢን ለማዘመን ERP ፕሮጀክትን ለመተግበር እየተሰራ እንደሆነ፤ የፉይናንስ እንዲሁም የኤርጎኖሚክስ ሪፎርም መከናወኑን በዚህም ምክንያት የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ በፍጥነትና በጥራት የማጠናቀቅ ስራ እየተከናወነ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የአስፋልት ንጣፍ፣ ህንፃና የአጥር እድሳት፣ ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ጊቢን የማስዋብ ስራም መሰራቱን ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ጠቁመዉ በዋነኝነት አቅርቦትን ለማሳደግ የሀገር ዉስጥ አምራቾችን የመደገፍ ስራ እየተከናወነ እንደሆነና በ2016 ዓ.ም 97 መድኃኒቶችን በሀገር ዉስጥ አምራቾች ለማምረት መታቀዱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
የመጋዘን አያያዙን በቴክኖሎጂ ማዘመን እንደሚገባ የገለፁት የምክርቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ሎሚ በዶ መንግስት የጤና ሴክተሩን ለመደገፍ ትኩረት በመስጠት የበጀት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡- አማኑኤል ወርቃየሁ
# ማገልገል ክብር ነው
