የ2014 በጀት ዓመት የህክምና ግብዓቶችና የመድኋኒት ፍላጎት ምጠና እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡==========================
ኤጀንሲው ለ2014 በጀት ዓመት የህክምና ግብዓቶችና የመድኋኒት ፍላጎት ምጠና እያካሄደ መሆኑን የግዥ ትንበያና ገበያ ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ በርሔ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም አስታወቁ፡፡የመድኋኒት ምጠናው ለጤና አገልግሎት የሚያስፈልጉትን የሕክምና መገልገያና መድኋኒት ብዛትና ወጪውን የመገመት ሂደት መሆኑንና የተመቻቸና የማያቋርጥ አቅርቦትን ለማረጋገጥ ትዕዛዞች መቼ መሰጠት እንዳለባቸው መወሰን ነው ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡አክለውም የመድኋኒት ምጠና የቁጥር ማረጋገጫ፣ የመድኃኒት አምራቾቹ የመጨረሻ መጠኖች እና ወጪዎች ሲወሰኑ የሚያበቃ የአንድ ጊዜ እንቅስቃሴ ሣይሆን ዓመቱን በሙሉ የሚሰራ እንደሆነ ገልጸዋል ፡፡ ዳይሬክተሩ በጤና ተቋማት በትክክል አመታዊ የመድኋኒት የፍጆታ መጠን የሚገልጽ መረጃ አለመኖሩና በቂ በጀት ሳይኖራቸው የህክምና ግብዓቶች እንዲቀርቡላቸው መጠየቃቸው ለኤጀንሲው አስቸጋሪ እንደሆነበት ተናግረዋል፡፡ምጠናው ዋናው መ/ቤት፣ ከቅርንጫፍ፣ ከጤና ተቋማት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመስራት የጋራ መግባባት ላይ እንደተደረሰና አዲሱን የመድሀኒት የግዥ መዘርዝር ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ አቶ ሀብቱ አብራርተዋል፡፡የድሬዳዋ ቅርንጫፍ የግዥ ትንበያና ገበያ ጥናት ቡድን መሪ አቶ ስማቸው ቀረብህ አመታዊ የመድኋኒት ምጠና ስራው በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ትንሽ ቢዘገይም ተረባርበን የጤና ተቋማትን በመደገፍ በጋራ ለመስራት ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡ጥንቃቄ የተሞላበት ምርጫ እጥረት፣ ትክክለኛ ያልሆነ የቁጥር፣ ከፍተኛ ዋጋዎች፣ የአገልግሎት ማብቂያ፣ ምክንያታዊ ያልሆነ ማዘዣና አጠቃቀም እና ሙስና ከመጀመሪያው ወጪ እስከ 70% የሚሆነውን የመድሀኒት ኪሳራ እንዲሁም ከ20-40% የሚሆነው በትክክል ካለመመጠን ጋር ብክነት እንደሚያስከትል የአለም ጤና ድርጅት ጥናት ያሳያል፡፡
አወል ሀሰን