ፈጣን ለውጥ አምጪ ለውጥ ማሣየቱ ተነገረ

የፈጣን ለውጥ አምጪ መሣሪያ መተግበር ከጀመረ በኋላ በአንዳንድ መድኃኒቶችና የህክምና ግብዓቶች ላይ ከ80 በመቶ በላይ መድኃኒቶችን ማቅረብ አስችሏል ተባለ፡፡
ኢኒሼቲቭ ከመተግበሩ በፊት ከግል ድርጅቶች ስናቀርብ የነበረውን መድኃኒት ከኤጀንሲው እንድናገኝ አድርጎናል ሲሉ የፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል የመድኃኒት ግብዓቶች አቅርቦት ኦፊሰር አቶ ጌትነት ውቡ ተናግረዋል፡፡
የኢኒሼቲቭ መጀመር በሆስፒታሉ እና በኤጀንሲው መካከል ግንኙነትና መረጃ ልውውጥ እድል ስለፈጠረ የምንፈልጋቸውን መድኃኒቶች በመጠየቅ ቶሎ ከቅርንጫፍ ማግኘት አስችሏል ብለዋል፡፡
ሪፈራል ሆስፒታሉ ያለበት የመድኃኒት ዱቤ ጫና በኢኒሼቲቭ እንዳይሣተፉ እክል እየፈጠረ መሆኑን ተናግረው ኤጀንሲው በዚህ መልኩ እገዛ ያድርግልን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
የባህርዳር ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አምሣሉ ጫኔ በአራት ትልልቅ ሆስፒታሎች ኢኒሼቲቭ መተግበራቸውን ተናግረው በቀጣይ የተሣታፊዎች ቁጥር ወደ 11 ከፍ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ኢንሼቲቨ ለመተግበር ሰባት ተጨማሪ የጤና ተቋማትን ማሰልጠናቸውን ገልጸው በቀጣይ የኢኒሼቲቭን አድማስ ከፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በኢኒሼቲቭ በሚደርሰን ሪፖርት መሰረት መድኃኒቶችን ከአንዱ ጤና ጣቢያ ወደ ሌላ በማዘዋወር ውጤታማ ሥራ መሰራቱን ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡
ኤጀንሲው መድኃኒቶችን የሚያቀርበው ከዱቤ ሽያጭ ከሚያገኘው ገቢ መሆኑን ገልጸው ተቋማት መድኃኒቶችን ለማግኘት በተገቢው መልኩ ገቢ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡
ከዝግጅት ክፍሉ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢኒሼቲቭ ከተጀመረ አምስት ወር እንደፈጀ ከኃላፊው አንደበት ሰምተናል፡፡ port�j=��y