ለማህፀን በር ካንሰር ህክምና አገልግሎት የሚውል የህክምና መሳሪያ ተሰራጨ

January 25, 2022Featured News
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ለማህፀን በር ካንሰር ህክምና አገልግሎት የሚውል የህክምና መሳሪያ ማሰራጨቱን የመድኃኒት ክምችትና ስርጭት ባለሙያ አቶ የቻለ ሽፈራው ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም አስታወቁ፡፡
የተሰራጨው የህክምና መሳሪያ Cryotherapy unit-Cervical ሲሆን 24 ሚሊየን 969 ሺህ 138 ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡
ስርጭቱም በኤጀንሲው ቅርንጫፎች አማካኝነት ለደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ ለጅጅጋ፣ ለሲዳማ፣ ለአማራ፣ ለኦሮሚያ፣ ለሶማሌ፣ለአፋር፣ለድሬደዋና ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የተካሄደ መሆኑን ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
ሂሩተ ኃይሉ