ለማህፀን በር ካንሰር መከላከያ የሚያገለግል ክትባት እየተሰራጨ መሆኑ ተገለፀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በጤና ፕሮግራም የሚገኝ ለማህፀን በር ካንሰር መከላከያ የሚዉል Human papilloma virus (HPV) ክትባት እየተሰራጨ መሆኑን በመጋዘን አያያዝ እና ክምችት ዳይሬክቶሬት የክትባት ተጠሪ አቶ ሃብታሙ አለማየሁ አስታውቀዋል፡፡
ከ394 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የክትባት መድኃኒቱ ከ1.6 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ልጃገረዶች ማስከተብ እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን ክትባቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ተያያዥ ግብዓቶች Syringe፣ Safety box እና Adrenalin injection እየተሰራጩ መሆኑን አክለዉ 469 ሚሊየን 166 ሺህ 338 ብር ወጪም ተደርጎባቸዋል፡፡
ክትባቱ እና ተያያዥ ግብዓቶች ከጤና ሚኒስቴር በተላከ የክፍፍል መርሀ-ግብር መሠረት በአገልግሎቱ 19ኙ ቅርንጫፎች አማካኝነት ለጤና ተቋማት ተደራሽ እየተደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከየካቲት 25 – 29 ቀን 2016 ዓ.ም በልዩ መልኩ እድሜያቸው 14 ዓመት ለሆኑ ታዳጊዎች በዘመቻ እንደሚሰጥ የጤና ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡
#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ
![](https://epss.gov.et/wp-content/uploads/2024/03/429657858_709507638004074_6307951655178643015_n-1-1024x836.jpg)