#ለስኳር ህክምና አገልገሎት የሚውሉ መድኃኒቶች ተሰራጩ

የኢትዮጲያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ለስኳር #ህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶችን ማሰራጨቱን የመድኃኒት ክምችት ባለሙያ ወ/ሮ ጤናዬ ተክሉ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም አስታወቁ፡፡የተሰራጭቱ መድኃኒቶች 250ሺ 91 እሽግ #Metformin -500mg-Tablet፣ 436ሺ 900 እሽግ Insulin Isophane Human-100IU/ ml in 10ml vial Injection እና 128ሺ 160 እሽግ Glibenclamide-5mg-Tablet ሲሆኑ ከሀምሌ 15 ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ መሰራጨቱን ወ/ሮ ጤናዬ ገልጸዋል፡፡#ስርጭቱም በኢትዮጲያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቅርንጫፎች አማካኝነት የተካሄደ ሲሆን በአጠቃላይ 17 ሚሊየን 182 ሺህ 198 ብር ወጪ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡በሁሉም አይነት ለስኳር ህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚውሉ በጥቅሉ 330ሺ 479 እሽግ ተጨማሪ መድኃኒቶች በክምችት እንደሚገኙ እና በግዥ ሂደት ላይም ያለ መኖሩን ባለሙያዋ ተናግረዋል ፡፡
ሂሩት ኃይሉ