ለቲቢ ምርመራ አገልግሎት የሚውል መመርመሪያ ኪት እየተሰራጨ እንደሆ ተገለጸ፡፡

September 22, 2021Featured News
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለቲቢ ምርመራ አገልግሎት የሚውል መመርመሪያ ኪት ከሀምሌ እስከ መስከረም ባሉት ወራት በተከታታይ እያሰራጨ መሆኑን ከመጋዘን አያያዝና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡የተሰራጨው መመርመሪያ ኪት ( Urine TB-LAM) የተሰኘ ሲሆን የበሽታ መከላከል አቅማቸው (CD4) ከ200 በታች የሆኑ የኤች አይቪ ህሙማን የቲቢ በሽታ በውስጣቸው መኖር፣ አለመኖሩን በቀላሉ በሽንት ለማረጋገጥ የሚረዳ መመርመሪያ መሆኑንን ለመረዳት ተችሏል፡፡
ስርጭቱም በኤጀንሲው ቅርንጫፎች አማከኝነት ለ1 ሺህ 500 የኤች አይቪ ምርመራ አገልግሎት ለሚሰጡ ጤና ተቋማት የሚካሄድ ሲሆን ወደ 6 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ዋጋ እንዳላው የዳይሬክቶሬቱ መረጃ ያሳያል፡፡