ለአስተማማኝ የመድኃኒት አቅርቦት ከሀገር ውስጥ አምራችና አቅራቢዎች ጋር መስራት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ኤጀንሲው ከ11 የሃገር ውስጥ የመድኃኒት አቅራቢዎች፣ ከጤና ሚኒስተር፣ ከንግድ ሚኒስቴር፣ ከባንኮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ሚያዝያ 6 ቀን 2013 ዓ.ም በራማዳ ሆቴል የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡
የሃገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾችና አቅራቢዎች ያሉባቸውን ችግሮች በመቅረፍ ለህዝቡ አስተማማኝነት የመድኃኒት አቅርቦት እንዲኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራት አንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለምፀሀይ ጳውሎስ ጥሪ አቅርበዋል።
የውጭ ምንዛሬ፣ የጥሬ እቃ ዋጋ መናር፣ የጥሬ እቃዎች ታክስ፣ አንዲሁም የአሰራርና የግብአት ችግሮች ተደማምረው በሙሉ አቅማችን አንዳናመርት አድርጎናል ሲሉ አምራቾች ተናግረዋል።የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አለምፀሀይ ጳውሎስ ባለድርሻ አካላት የሀገርን ውስጥ መድኃኒት አቅራቢዎችን በራሳቸው ጥረት ብቻ ውጤታማ መሆን እንደማይችሉና ሁሉም ባለድርሻ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊወስድ ይገባል ብለዋል።በአሁን ወቀት ከሀገር ዉስጥ አምራቾች ከ20% የማይበልጥ የመድኃኒት አቅርቦት ነው እየተገኘ ያለው ፥ ይህ እጂግ በጣም አሳሳቢ ነው ብለዋል።
በተያያዘ ዜና ለአምራቾቹ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ መድኃኒት አንዲያመርቱ የተቀናጀ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ሲሉ የንግድ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተካ ገ/ኢየሱስ ገልፀዋል።አክለውም ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ያለቁና የተፈቀደላቸው መድኃኒቶች ከታክስ ሙሉ በሙሉ ነፃ እንደሆኑ አስታውሰው መድኃኒት ለመሥራት በሚውሉ ጥሬ አቃዎች ላይ ታክስ የሚጠይቅበት አሠራር ካለ መታየት እንዳለበት አብራርተዋል።