#ለአእምሮ ህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች መሰራጨታቸው ተገለጸ

የኢትዮጵያ #መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከሀምሌ 15 እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም ለአእምሮ ህሙማን #ሕክምና አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶችን ማሰራጨቱን የክምችትና ስርጭት ባለሙያ አቶ አብዱራህማን አይረዲን አስታወቁ፡፡ኤጀንሲው ከ29 በላይ መድኃኒቶችን ያሰራጨ ሲሆን ከእነሱም መካከል #Carbamazepine, Phenytoin (Diphenhydantion) sodium, Fluoxetine, Haloperidol, Resperidone, እና Trifluoperazine እንደሚገኙበት ባለሙያው ተናግረዋል፡፡#ስርጭቱም በኤጀንሲው ቅርንጫፎች አማካኝነት የአእምሮ ህክምና መስጫ ጤና ተቋማት የተካሄደ ሲሆን 34 ሚሊየን 477 ሺህ 239 ብር ወጪ እንደተደረገባቸው ባለሙያው አብራርተዋል ፡፡