ለአጥንት ስብራት ጥገና ህክምና አገልግሎት የሚውሉ የorthopedic መሳሪያዎች እየተሰራጩ መሆኑ ተገለጸ

January 25, 2022Featured News
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ለአጥንት ስብራት ጥገና ህክምና አገልግሎት የሚውሉ የOrtho Pendic ህክምና መሳሪያዎችን ከህዳር 13 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በማሰራጨት ላይ እንደሆነ የመድኃኒት ክምችትና ስርጭት ባለሙያ አቶ የቻለ ሽፈራው ጥር 16 ቀን 2014 ዓ.ም ገለጹ፡፡
የአገልግሎት ተቋሙ ከሚያሰራጫቸው የOrtho Pendic የህክምና መሳሪያዎች መካከል k wire, SET-DRILL BIT, Set- power drill, set- locking 3.5mm, Set locking bolts, plate- narrow L.C.D 4.5MM, set- External Fixeter large እና ሌሎችም እንደሚገኙ አቶ የቻለ ገልጸዋል፡፡
ስርጭቱም 15 ለሚሆኑ ትልልቅ የመንግስት ጤና ተቋማት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተካሄደ ሲሆን 6 ሚሊየን 808 ሺህ 245 ብር የሚገመት ወጪ እንደተደረገባቸው ባለሙያው ተናግረዋል ፡፡
ሂሩት ኃይሉ