ለኤጀንሲው ቅርንጫፎች ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

September 9, 2019ፊውቸርድ ዜና
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከነሐሴ 28–30/2011 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ባደረገው 3ኛው የአቅርቦት ሠንሠለት የውይይት መድረክ 4 የኤጀንሲው ቅርንጫፎች ተሸላሚ ሆኑ፡፡
ተሸላሚዎቹ ሐዋሣ፣ ደሴ እና ሠመራ ቅርንጫፎች ሲሆኑ የተሸለሙበት ምክንያትም በልህቀት ማእከል ትግበራ እና ዓመታዊ የመድኃኒት ቆጠራን በወቅቱ አጠናቀው ለማህበረሠቡ አገልግሎት በመስጠታቸው እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል፡፡
በተያያዘ ዜና የአዳማ ቅርንጫፍ 2011 በጀት ዓመት በልዩ ተሸላሚነት የክሪስታል ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በመጨረሻም በቀጣይ በጀት ዓመት ሁሉም ቅርንጫፎች ልክ እንደ አዳማ ልዩ ተሸላሚ ለመሆን ተግተው እንዲሠሩ ከመድረኩ መልእክት ተላልፏል፡፡