ለኮሌራ በሽታ የክትባት መድኃኒት ለትግራይ ክልል እየተሰራጨ መሆኑ ተገለጸ፡፡

June 15, 2021Featured News
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለትግራይ ክልል የኮሌራ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የኮሌራ ክትባት መድኃኒቶችን በማሰራጨት ላይ እንዳለ በኤጀንሲው የመጋዘን አያያዝ እና ክምችት አስተዳደር ባለሞያ ወ/ሮ ማስተዋል አበባው ሰኔ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ገለጹ፡፡ ኤጀንሲው የሚያሰራጨው የክትባት መድኃኒት Oral Cholera Vaccine እንደሆነና 1 ሚሊየን 999 ሺህ 953 ዶዝ መጠን እንዳላቸው ሲሆኑ አንድ ዶዝ ለ አንድ ሰው ማስከተብ እንደሚያስችል ባለሞያዋ ተናግረዋል፡፡የክትባት መድኃኒቶቹ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 13 ወረዳዎች በኤጀንሲው ቅርጫፎች አማካኝነት የሚሰራጭ ሲሆን 173 ሚሊየን 155 ሺህ 930.74 ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል።