ለፅኑ ህሙማን መተንፈሻነት አገልግሉት የሚሰጡ 180 መካኒካል ቬንትሌተሮች በመሠራጨት ላይ መሆናቸው ተገለጸ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የአዳማ ፕሮጀክት ለፅኑ ህሙማን መተንፈሻነት አገልግሉት የሚሰጡ 180 መካኒካል ቬንትሌተሮችን ከመጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እያሰራጨ መሆኑን የአዳማ ማዕከላዊ የህክምና መሳሪያዎች መጋዘን ቡድን መሪ አቶ ደበበ ገበየሁ ገለፁ።
ስርጭቱም በአዳማ ፕሮጀክት አማካኝነት ለሚኒሊየም አዳራሽ የኮቨድ19 ህክምና ማዕከል ፣ ለየካ ኮተቤ ፣ ለፊልድ የኮቨድ19 ህክምና ማዕከል ሆስፒታል፣ ለጴጥሮስ፣ ለጳውሎስና ለአቤት ሆስፒታሎች የተሰራጬ ሲሆን በአጠቃላይ 41 ቬንትሌተሮች መሰራጨታቸውን አቶ ደበበ ገልፀዋል።ቬንትሌተሮቹ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ያለውን ኮቨድ19 ለማከም የሚረዳ መሆኑን አብራርተዋል።በቀጣይም ለአፋር፣ለአማራ፣ለኦሮሚያ ፣ለሶማሌ፣ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ለቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ለጋምቤላ፣ለሀረሪ ክልሎችና ለድሬደዋ ከተማ መስተዳድር ስርጭቱ እንደሚካሄድ ቡድን መሪው ተናግረዋል።በመሠራጨት ላይ ያሉት ቬንትሌተሮች ከኮርያ መንግስት በተገኘው ብድር ከሌሎች ኮቨድ19 ለመከላከል ና ለመቆጣጠር የተገዙ የህክምና መሣሪያ ናቸው ።
ቬንትሌተሮቹን ከኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ እስከነሙሉ አክሰሰሪያቸው እንደተረከቡ እና በባለሙያ ተገጣጥመው ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚደረጉ እንድሁም ጠቀሜታቸው በተለይ በአሁኑ ወቅት እጅግ አስፈላጊ እንደሆኑ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ የፊርማሲ ሜድካል ኢንስቱርመንት ስቶር ተወካይ ሀላፊ የሆኑት አቶ ዳዊት ታምሬ ተናግረዋል።
ሂሩት ኃይሉ