ለ3 ዓመት በማእቀፍ የተገዙ ሪኤጀንቶች ስርጭት እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ኤጀንሲው በማእቀፍ ግዥ /placement/ 37 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አድርጎ የገዛቸውን የቤክ ማን፣ ሲስ ሜክስ እና ኬሚስትሪ ማሽን የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች ስርጭት እያካሄደ እንደሚገኝ የክምችት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ሮ ሚዛን ገ/ዮሐንስ ገለፁ፡፡
እንደ ባለሙያዋ ገለፃ 27 ቤክ ማን ሲቢሲ ማሽን በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮምያ እና በደቡብ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ለሚገኙ ሆስፒታሎች የማሽኖቹ ተከላ ተከናውኖ የሪኤጀንት ስርጭት እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል፡፡
10 የቤክማን ሲቢሲ ማሽኖች አዲስ አበባ ላይ ለሚገኙ ዘውዲቱ፣ የካቲት፣ ምንሊክ፣ ጦር ኃይሎች፣ አለርት፣ አቤት፣ ዼጥሮስ፣ ጥቁር አንበሣ እና ዻውሎስ ሆስፒታል የሕክምና መሣሪያው ተከላ መካሄዱንና ሁሉም ስራ መጀመራቸውን ወ/ሮ ሚዛን አስታውቀዋል፡፡
አያይዘውም 14 የኬሚስትሪ /ሮሽ ወይም ኮባስ/ የተሠኘ ማሽን እና 2 የሲስ ሜክስ ሲቢሲ ማሽኖች ለጤና ተቋማት ስርጭት መካሄዱንና የሪኤጀንትም ስርጭት ተካሂዷል ሲሉ ባለሙያዋ ገልፀዋል፡፡
ባለሙያዋ የማእቀፍ ግዥ መከናወኑ ሪኤጀንቶቹ በጥራትም፣ በዋጋም ቀድሞ ከነበረው የተሻሉ እንደሆነ አስታውቀው የ3 ዓመት ግዥ በመፈፀሙ ከዚህ በኋላ የሪኤጀንትን መቆራረጥ እንደሚያስወግድ አስረድተዋል፡፡
የሲ.ቢ.ሲና የኬሚስትሪ ማሽን በደማችን ውስጥ ያለውን የደም ሕዋሣት መጠንን የሚለካ መሣሪያ እንደሆነና የመሣሪያዎቹ መተከል ማህበሠረቡን ከአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንደሚታደግና ከዚህ ቀደም የነበረውን የጤና ተቋማት ቅሬታንም ይፈታል ሲሉ ወ/ሮ ሚዛን ተናግረዋል፡፡