ማዕከላዊ ክላስተር 94% የመድኃኒትና የህክምና መገልገያዎች ስርጭት ማካሄዱን አስታወቀ፡፡

በኤጀንሲው የማዕከላዊ ክላስተር በ2011 በጀት ዓመት 94% የመድኃኒትና የህክምና መገልገያዎች ስርጭት ማካሄዱን ነሐሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. በ3ተኛው የአቅርቦት ሠንሠለት መድረክ ላይ ተገለፀ፡፡
የአዲስ አበባ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ሞገስ በማዕከላዊ ክላስተር አዲስ አበባ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ በበጀት ዓመቱ በመደበኛውና በፕሮግራም መድኃኒት 1.7 ቢሊየን ብር ለማሠራጨት አቅዶ የ1.9 ቢሊየን ብር (107%) እንዳሠራጨ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ቁጥር 2 ቅርንጫፍ የ730 ሚሊየን ብር መድኃኒት ለማሠራጨት አቅዶ 454 ሚሊየን ብር (62.24%) ማሠራጨቱንና አጠቃላይ የክላስተር አፈጻጸሙም 94% መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡
በማዕከላዊ ክላስተር አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በማዕከላዊ ክላስተር 73 ሆስፒታሎችና 452 ጤና ጣቢያዎች ተጠቃሚ እንደሆኑና 87 ጤና ጣቢያዎችና 21 ሆስፒታሎች ቀጥታ የክትባት መድኃኒቶች እንደሚያገኙ ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡
በበጀት ዓመቱ ለጤና ተቋማት በዱቤ ከተሠጠ 823 ሚሊየን ብር የሚያወጡ መድኃኒቶች ውስጥ 614 ሚሊየን ብር መሠብሠቡንና 74.6% መሆኑን አቶ ሙሉቀን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ሣይሠበሠብ የቀረና ወደ 2010 በጀት ዓመት የዞረ ያልተሰበሰበ ሂሳብ 564 ሚሊየን ብር 280 ሚሊየን ብር መሠብሠቡንና በመቶኛም 49.7% መሆኑ ተገልጿል፡፡
ክላስተሩ በሆስፒታሎች ያለውን የመድኃኒት አቅርቦት ለማሻሻል የፈጣን ለውጥ አምጪ ኢኒሼቲቭ መተግበሩን በሪፖርቱ ተናግረዋል፡፡
ለ2011 በጀት ዓመት ከተመደበ የገንዘብ መጠን 11.2 ሚሊየን ብር በዓመቱ ሥራ ላይ የዋለ የገንዘብ መጠን 7 ሚሊየን ብር በፐርሠንትም 72% እንደሆነ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
በበጀት ዓመቱ ለጤና ተቋማት በዱቤ የሚሰራጩ የህክምና ግብዓቶችን ሂሣብ በጊዜ ያለመሰብሰብ ችግር እንዳጋጠማቸው ሪፖርቱ ያሣያል፡፡