ሠመራ ቅርንጫፍ 81.5 ሚሊዮን ብር የጤና ፕሮግራም ግብኣቶች ስርጭት ማድረጉን ገለጸ፡፡ ==================================================

October 8, 2019news
በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የሠመራ ቅርንጫፍ ባሳለፍነው በጀት ዓመት የጤና ፕሮግራም ግብዓቶችን ማሰራጨት እንደቻሉ የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱላሂ አብዱሺሃም ገልጸዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ መድኃኒቶች፤ ኬሚካልና ዲያግኖስቲክስ እንዲሁም የህክምና መገልገያዎችና መሳሪያዎች 75,801,939 ብር ስርጭት ለማድረግ አቅደው 81,560,601.15 ብር ለአፋር ክልል ማሰራጨታቸውን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
የሠመራ ቅርንጫፍ በክልሉ ውስጥ ለ 5 ሆስፒታሎች፣ ለ64 ጤና ጣቢያዋችና 32 ወረዳ ጤና ጽ/ቤቶች በቀጥታ የሚደርስባቸው ተቋማት እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡
ሠመራ ቅርንጫፍ በ2011 በጀት ዓመት በልህቀት ማእከል ትግበራና ዓመታዊ መድኃኒት ቆጠራ 77% በማግኘት የ 3ተኛ ደረጃ ይዞ ከኤጀንሲው እውቅና እንደተሰጠው ይታወሳል፡፡
Supply chain of compassion!!!