ሣንሸንግ ፋርማሲዩቲካል የግል ኩባንያ ለኮቪድ 19 ቅድመ መከላከል የተለያዩ የህክምና ግብዓቶችን ድጋፍ አደረገ፡፡

May 7, 2020ፊውቸርድ ዜና
ሳንሸንግ ፋርማሲዩካል የተባለ የግል ኩባንያ ሚያዝያ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ለኮቪድ 19 ቅድመ መከላከል የተለያዩ ግብዓቶችን ድጋፍ ማድረጉን የመጋዘን አያያዝና ክምችት ባለሙያ ወ/ት ኑሃሚን ኤልያስ ሚያዝያ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ገለፁ፡፡
እንደ ባለሙያዋ ገለፃ ኩባንያው 1 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው 290 የእጅ ሣኒታይዘር (Alcohol based hand Sanitizer)፣ 1400 ኬሚካል (Sansafe 84-environmental Disinfectant)፣ 8 /ለኮሮና መከላከያ የመድኃኒት መርጫ (Spray Bucket with Pump) በጤና ሚኒስቴር በኩል ድጋፍ የተሰጠ ሲሆን ወደ ኤጀንሲው መጋዘን ገብቷል፡፡