ሹፌሮችን ለመጥቀም የተዘጋጀ መለኪያ ነጥብ ነው ተባለ

በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች የመገኛ ቦታ ጠቋሚ መሣሪያ (GPS) ሙሉ በሙሉ ውጤታማ እንዲሆን በአሽከርካሪዎች ማበረታቻ መመሪያ ላይ ያሉ የመለኪያ ነጥቦች እንዲሻሻል ሲጠይቁ መመሪያው ሁሉንም ተጠቃሚ ለማድረግ ነው ሲሉ የኤጀንሲው ኃላፊ መልስ ሰጡ፡፡
የአዩ ቴክኖሎጂ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳኛቸው ይምሩ ሐምሌ 13 ቀን ስለ መገኛ ቦታ መሣሪያ ባደረጉት ገለጻ “የተዘጋጀው መስፈርት ጥሩ ሆኖ የመለኪያ ነጥቦችን ዝቅ ማድረግ የመሣሪያውን ውጤታማነት ይቀንሰዋል” ብለዋል፡፡
ሥራ አስኪያጁ የመለኪያ ነጥብ ከ90 በመቶ በላይ ባለው መጠቃለል እንዳለበት ጠቁመው እስከአሁን ባለን የGPS ሪፖርት በቀላሉ ማንኛውም አሽከርካሪ የሚደርስበት ነጥብ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ዳኛቸው የመመዘኛ ውጤት እስከ 59 በመቶ ዝቅ ማለቱ አሽከርካሪዎች ጥፋት እያጠፉ እንኳን እንደማበረታታት የሚቆጠር ነው ብለዋል፡፡
የመኪናውን ደህንነትና ሀብት በተጨማሪም የሹፌሮች የጊዜ አጠቃቀም ከፍ ለማድረግ መስፈሪያው ሊከለስ ይገባል ሲሉ ምክረ- ሃሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዓለም አድራሮ መመዘኛ መስፈርቱ አሽከርካሪዎችን ለመጥቀም እና ያለውን ጫና ለማቃለል ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
መስፈርቱ ሁሉም ስለተጣጣሩ የሚያገኙትና ከዚህ በፊት ከኪሳቸው የሚያወጡትን ወጪ ለማስቀረት ታስቦ የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተያያዘ ዜና አቶ ዳኛቸው ሐምሌ 14 ቀን ባደረጉት ቃለ ምልልስ GPS በኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ ምክንያት የመረጃ ልውውጥ ቢቋረጥም መሣሪያው መረጃዎችን በማስቀመጥ አገልግሎቱ ሲመለስ መረጃውን ቀስ በቀስ ይልካል ብለዋል፡፡
አክለውም የኢንተርኔት መቆራረጥን ለመቅረፍ ከቴሌ ኮሙኒኬሽን ጋር እየሠሩ መሆኑን ተናግረው እንዳማራጭ የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት መጠቀም እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡
በመሣሪያው ላይ አደጋ አድርሶ ትርፍ ለማትረፍ የሚንቀሳቀስ ቢኖር ሊደርስ የሚችለው ጉዳት ከመሣሪያው በሚቀርብ ሪፖርት መሠረት እንደሚጋለጥ አስታውቀዋል፡፡ �j=��