ቅርጫፉ በ2014 በጀት አመት የላቀ አፈጻጸሞች ለነበራቸውየእውቅና እና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጠ።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የአዳማ ቅርንጫፍ በ2014 በጀት ዓመት በቅርንጫፉ ለተመዘገቡ በርካታ ክንውኖች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሠራተኞች የእውቅና እና የምስጋና ምስክር ወረቀት መስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም ተሰጠ።
የዋና ዳይሬክተር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ እንግዳየሁ ደቀባ በመረሃ ግብሩ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የአዳማ ቅርንጫፍ የላቀ የስራ አፈጻጸም በማስመዝገብ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት ቅርንጫፎች አንዱ እንደሆነና ለሌሎችም አርአያ እንደሚሆን ገልፀው በቀጣይ ቅርንጫፉ ሊያከናውናቸው በዕቅድ በያዛቸው ጉዳዮች የዋና መ/ቤት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
ዓላማው በ2014 ዓ.ም ለተመዘገቡ መልካም አፈጻጸሞች ሠራተኛው ለተጫወተው ጉልህ ሚና የምስጋና እና እውቅና ምስክር ወረቀት ለማበርከት እንዲሁም የተሰሩ ስራዎችን ለማስመረቅ እንደሆነ የቅርንጫፉ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ወርቅነህ አበበ ገልፀዋል።
አቶ ወርቅነህ አክለውም ትጉህ ሠራተኛን ማመስገንና ማበረታታት በሌሎች ሠራተኞች ላይ የተነሳሽነት ስሜት እንዲፈጠርና በቀጣይ ለታቀዱ ስራዎች የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
በቅርንጫፉ በ2014 ዓ.ም በISO 90001: 2015 የጥራት ሠርተፊኬት እና የዓመታዊ ቆጠራን በአንድ ቀን ተኩል በማጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሠራተኞች እንዲሁም ከቅርንጫፍ ጎን በመሆን የተለያየ ድጋፍ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት የምስክር ወረቀት የተበረከተ ሲሆን በተለያየ ምክንያት መስሪያ ቤት ለቀየሩና በጡረታ ለተገለሉ ሠራተኞች የአልባሳት ሽልማት ፣ በተጨማሪም ለዘማች ቤተሰብ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።
በዕለቱ የተቋሙ የማኔጅመንት ዓባላት የቅርንጫፍ የሴቶችና ወጣቶች ፎረም ከማኔጅመንቱ ጋር በቅንጅት የተሰሩ የቢሮ የማስዋብ፣ ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር፣ የጓሮ አትክልትና የመሳሰሉትን ስራዎች በመዘዋወር ጎብኝተው አድናቆታቸውን ቸረዋል።
በመርሃ ግብሩ የዋናው መ/ቤት የማኔጅመንት አባላት ፣የቅርንጫፉ ሀላፊዎችና ሠራተኞች ተሳትፈዋል ።