በመጪው ጥር ወር 3.1 ሚሊየን አጎበሮች እንደሚሠራጩ ተገለፀ፡፡

January 17, 2020ፊውቸርድ ዜና
ኤጀንሲው ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በመጪው ጥር ወር 3.1 ሚሊየን ብዛት ያላቸው አጎበሮች ለጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል እና ደቡብ ክልሎች እንደሚያሠራጭ ከታህሣስ 18 – 19/2012 ዓ.ም. በተካሄው ኦረንቴሽን ላይ ተነግሯል፡፡
የአጎበር ስርጭቱ ከጥር 23/2012 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን አጎበር ለወባ መከላከያነት አገልግሎት የሚውል ግብዓት መሆኑን ከስርጭት እና ተሽከርካሪ ስምሪት ዳይሬክቶሬት ባገኘነው መረጃ ተገልጿል፡፡