በአገልግሎቱ ዓለም-አቀፍ የሴቶች ቀን ተከበረ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም አቀፍ ለ114ኛ በኢትዮጵያ 49ኛ ጊዜ ከየካቲት 21 – መጋቢት 18 << ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል >> በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ሲሆን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትም በዓሉን አክብሯል፡፡
ሴቶች በምንሳተፍበት ዘርፍ ሁሉ አመርቂ ውጤት የምናስመዘግብ በመሆናችን አለም አቀፋዊ የሆኑ ለውጦች ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከት እንችላለን ያሉት የመጋዘን አያያዝና ክምችት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ገዳምነሽ አስፈራው ወደ ፊት ለሚመጡ ልጆቻችን የፆታን እኩልነትን እያስተማርን የማሳደግ ኃላፊነት አለብን ሲሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
በአገልግሎቱ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ባለፉት ስድስት ወራት የተሠሩ ስራዎች ሪፖርት የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ወ/ሮ አለምፀሐይ ዳታ የቀረቡ ሲሆን የህፃናት ማቆያ መቋቋም እና ሌሎቹ አንኳር ተግባራትን ቀርበዋል፡፡
የሴቶች ቀን መከበር የተጀመረበትን ታሪካዊ አመጣጥ፣ ዓላማ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ መከበሩ ያመጣቸውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጦች እንዲሁም የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ሚና ከማሳደግ አንፃር የተሰሩ ስራዎችና ከሴቶች ምን ይጠበቃል የሚለውን የሴቶች ጉዳይ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ኤፍሬም ግርማ በዝርዝር አቅርበዋል።
በመጨረሻም እለቱን በማስመልከት የጡት እና የማህፀን ጫፍ ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ከቸርችል ጤና ጣቢያ በመጡ ባለሙያዎች የተሠጠ ሲሆን የማህፀንና የጡት ካንሠር ምርመራ እንዲሁም የደም ልገሳ መርሀ ግብር ተካሂዷል ።
