በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መረጃ ማዕከልና በኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የህክምና ግብአቶች የግዥ ውል ተፈረመ።

September 13, 2021Magazine
በኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ እና በኢትዮጵያ #የልብ ህሙማን ህፃናት መረጃ ማዕከል መካከል ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ለህፃናት የልብ ህሙማን የሚውሉ የህክምና ግብአቶች የግዥ ውል ጳጉሜ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ተፈርመዋል።የህክምና ግብአቶች የሽያጭ ውል ስምምነቱን በኤጀንሲው በኩል ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እና በልብ ህሙማን መርጃ በኩል የማእከሉ ሜድካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሳምሶን አደራ ፈርመዋል ።በተደረገው ስምምነት መሰረት ኤጀንሲው ከ 6 ወራት ውስጥ ለህፃናት የልብ ህሙማን የሚውሉ የህክምና መድሀኒቶቹን፣ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች፣ አላቂ እቃወች እና የላቦራቶሪ ግብአቶችን እንደሚያቀርብ በውሉ ተመላክቷል።በማእከሉ በኩል የግብአቶችን የግዥ ሂደት ለማስጀመር 30% ለኤጀንሲው ገቢ የሚደረግ ተገልጿል።እስከዛሬ በኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በኩል ለተደረገላቸው እና እየተደረገላቸው ላለው መልካም ትብብር ምስጋና ያቀረቡት በልብ ህሙማን መርጃ የማእከሉ ሜድካል ዳይሬክተሩ ዶ/ር ሳምሶን አደራ ሲሆኑ የተደረገው ስምምነት በልብ ህመም ለሚሰቃዩ እና ለመታከም ወረፍ እየጠበቁ ለሚገኙ ህፃናት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
አወል ሀሠን