በኢንግሊዝ መንግስት እና በዩኒሴፍ በጋራ ትብብር ድጋፍ የተደረጉ የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የህክምና ግብዓቶች ርክክብ ተፈጸመ

May 7, 2020ፊውቸርድ ዜና
በኢንግሊዝ መንግስት እና በዩኒሴፍ ድጋፍ በጋራ ትብብር የተደረጉ የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የህክምና ግብዓቶች የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና የዩኒሴፍ ተወካይ በኢትዬጵያ አደል ኮድር በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ መጋዘን በመገኘት ዛሬ ሚያዝያ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ርክክብ አደረጉ፡፡
ድጋፍ የተደረጉት የህክምና ግብዓቶች N95 የፊት እና የሰውነት መሸፈኛ ጭምበልን ጨምሮ ለኮሮና በሽታ ለመከላከል የሚስችሉ ግብዓቶች መሆናቸው በርክክቡ ወቅት ተገልጾል፡፡
ዶ/ር ሊያ በበኩላቸው በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ድጋፍ መደረጉ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ያለውን ዝግጁነትና ምላሽ ሰጭነት የሚረዳ እና ጤና ባለሙያዎች ያለምንም ስጋት ለማከም እንዲችሉ እጅግ ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸው የተደረገልን ድጋፍ እጅግ አድርገን እናመስግናለን በማለት ገልጸዋል፡፡
የዩኒሴፍ ተወካይ በኢትዮጵያ የሆኑት አደል ኮድር በበኩላቸው ይህ እገዛ የመጀመሪያ መሆኑን ገልጸው ድጋፉ የሚቀጥል መሆኑን በርክክቡ ወቅት ተናግረዋል፡፡