በኤጀንሲው ወረቀት አልባ የሆነ የምዘና ስርዓት ለመተግበር የሚያስችለውን አውቶሜሽን ስራ ላይ ለማዋል ይረዳው ዘንድ ለአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከአሁን በፊት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ መሰረት EPSA PMS የተባለውን አውቶሜትድ ወረቀት አልባ የሆነ ለሠራተኞች ምዘና የሚውል ስርዓት ለመተግበር የአሰልጣኞች ስልጠና ከግንቦት 23-29 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሰጥቷል።የምዘናው ስርዓት ሠራተኞች የኤጀንሲውን ግቦች ተረድተው የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ከማስቻሉም ባሻገር ወጪና ጊዜ ቆጣቢ እንደሆነ ፣እንዲሁም ሠራተኞች በስራ አፈጻጸማቸው ልክ ውጤት የሚያስገኝ በመሆኑ እርካታ ሊሰጥ የሚያስችል አሰራር መሆኑን የኤጀንሲው የእቅድ ክትትል አና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ፀጋ ገልጸዋል።የEPSA PMS ዋና ዓላማው የኤጀንሲውንና የሠራተኛውን አቅም ማሳደግና የላቀ ውጤት አፈፃፀም ያለው ተቋም/High performing and learning organization /በመፍጠር ውጤታማ የሆነ ሠራተኛና ተቋም መገንባትነው ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።ስልጠናው ከዋናው መስሪያ ቤት እና ከቅርንጫፎች ከተውጣጡ የአሰልጣኞች ስልጠና (TOT)በሁለት ዙር የሚሰጥ እንደሆነ ከ አቶ ጌታቸው ማብራሪያ መረዳት ተችሏል ።ከሚቀጥለው ሐምሌ ወር ጀምሮ ሥራ ላይ የሚውለው EPSA PMS የሠራተኞች የምዘና ስርዓት ወጥ የሆነ የሪፖርት፣የውጤት አሞላል እንዲኖር ከማስቻሉም በላይ በሠራተኞችና በሀላፊዎች መካከል በቀላሉ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲኖር ያስችላል።በኢትዮጵያ አየር መንገድ የICT ክፍል የቢዝነስ ኤክስፐርት ባለሞያ የሆኑት አቶ መስፍን አባተ እንደተናገሩት ሶፍት ዌሩ የይለፍ ቁልፍ የተሰጠውን በማስተር ዳታ፣ ቁልፍ የውጤት አመልካች (KIP) ፣ ግብና ዓላማዎች ፣መለኪያዎች፣ ሊደረስበት የታሰበው ግብ(ታርጌት)፣ ተከታታይ የውጤታማነት መከታተያ ፣ግለ ግምገማ ማድረጊያ፣ የማጠቃለያ ውጤት፣ግብረ መልስመስጪያ፣የግል(self)፣የቡድን( team) የመሳሰሉ መገለጫዎች ያሉት ሲሆን አዳድስ መረጃወችን በየጊዜው ለመጨመርም ሆነ ወቅታዊ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ለዋና መ/ቤቱ እና ለቅርጫፎቹ የሚያገለግል በቪድዮ የተቀነባበረ መመሪያ ያለው ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ በይለፍ ቃላቸው መግባት የተፈቀደላቸው የማኔጅመንት አባልና ያልሆኑት ሠራተኞች የሚጠቀሙበት እንዲለማ የተደረገ ሶፍት ዌር ነው ብለዋል።ከባህርዳር ቅርንጫፍ የእቅድ ክትትል አና የግምገማ ባለሞያ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ዋለልኝ በስልጠናው ማስተር ዳታ እንዴት እንደሚዘጋጅ ፣የሠራተኞችን አፈጻጸም ውጤት አሰጣጥ፣የሁለትዮሽ ግንኙነትን እንዴት በሶፍት ዌሩ መጠቀም እንደሚቻል ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀው ለኤጀንሲውም የወረቀት አሰራርን በማስቀረት ብክነትን የሚቀንስ ፣ወጪና ጊዜ ቆጣቢ ከመሆኑም ሌላ ሠራተኞው ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዘመናዊ የአሰራር ዘዴን እንዲያዳብር ያግዛል ሲሉ ተናግረዋል።
ሂሩት ኃይሉ