በጦርነት ጉዳት የደረሰበትን የአምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መልሶ ለማቋቋም በማሰብ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት 1.4 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን የህክምና መሳሪያዎችን በነጻ ሰጠ፡፡

በአማራ ክልል ዋግ ኸምራ ዞን በጦርነት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን አምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራ ለማስጀመር የሚያስችለውን 53 አይነት 1.4 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸውን የህክምና መሳሪያዎች ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በነጻ የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም አግኝቷል፡፡የአገልግሎት ተቋሙ በሽያጭ በመደበኛነት ለጤና ተቋማት ከሚያቀርባቸው የህክምና መሳሪያዎች በጦነት ከተጎዱት አንዱ ለሆነው አምደወርቅ ሆስፒታል ማኔጅመንቱ ወስኖ ሲሰጥ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት አንዱ ማሳያ ሲሆን ሌሎችንም በጦርነቱ ለወደሙ የጤና ተቋማትን የማቋቋም ስራ ከጤና ሚንስቴር ጋር በመተባበር እንደሚሰራ ተገልጻል፡፡የሆስፒታሉን ስራ ለማስጀመር ዛሬ የተሰጠን የህክምና መሳሣሪያዎች ከአገልግሎት ተቋሙ ጋር በመነጋገር ፍላጎታችን መሰረት ያደረገ ድጋፍ ነው የተደረገልን ያሉት የአምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ብርሃኑ አለሙ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆኑ/vital /ግብአቶችን ስለተለገሳቸው ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ዶ/ር ብርሃኑ አክለውም የአግልግሎት ተቋሙ ከአሁን በፊት ከወረራው ነጻ በወጣን ማግስት የ1.2 ሚሊዮን ብር መድኃኒቶች እና የህክምና መገልገያዎችን በራሳቸው መኪና አጓጉዘው በማቅረብ ለወገን ደራሽነታቸውን አሳይተውናል ብለውል፡፡አምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ142 ሽህ የዋግኸምራ ህዝቦች ለ 33 ቀበሌዎች በወር በአማካኝ ለ2 ሺ 700 ህሙማን የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ የመጡት የህክምና መሳሪያዎች የአንድን ታካሚ ግፊቱን ፡የስኳር መጠኑን ፡ ለእናቶች እና ህጻናት ህክምና እንዲሁም ለመመርመሪያ የሚያገለግሉ መሳሪያዎች በመሆናቸውጠቀሜታቸው የላቀ ነው ብለዋል፡፡ ለሆስፒታሉ ተላኩትን የ 1.4 ሚሊዮን ብር ልዩ ልዩ የህክምና መሳሪያዎች በጦርነቱ ለተጎዳው ሆስፒታል በማስረከባችን ደስተኖች ነን ያሉት ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የመድኃኒት እና የህክምና ግብቶች ስርጭት እና ስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ እንዳለው አስማማው ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት በሚቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት መልሶ የማቋቋም ስራውንም ሆነ ሌሎች መደበኛ ስራዎችን በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡በህክምና መሳሪያዎች ርክክብ ላይ የአምደወርቅ ከተማ ከንቲባ፡የአካባቢው አስተዳር ሀላፊዎች የአገው የሀገር ሽማግሌውች ተገኝተው መልክት ያስተላለፉ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ በህዝቡ ስም ምስጋና አቅርበዋል ፡ለሆስፒታሉ ሙያተኞችም የስራ ተነሣሽነታቸውን እንሚጨምርላቸው ተገልጿል ፡፡
አወል ሀሰን