አገልግሎቱ በባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት በረመዳን የመጨረሻው ቀን የኢፍጣር ፕሮግራም ተደርጓል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ ለሚደረግላቸው ዜጎች መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የኢፍጣር መርሀ ግብር አካሂዷል ።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ በባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት ተገኝተው ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል ዋዜማ በሠላም አደረሳችሁ በማለት መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን የበጎ አድራጎት ድርጅቱን አባላት አስፈጥረዋል፡፡
ወ/ሮ ፍሬህይወት ይህንን የረመዳን የኢፍጣር ፕሮግራም ላዘጋጀው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በዚህ በረመዳን ወር ያለው ለሌለው የማከፈል እና የመረዳዳት እሴት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የዘንድሮውን ረመዳን የመጨረሻ ኢፍጣር በባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት አብረናችሁ በማሳለፋችን ደስተኛ ነን ያሉት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ በቀጣይም ማንኛውም ድጋፍ በሚያስፈልግበት ጉዳይ ከጎናችሁ ነን ብለዋል ።
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች በዛሬው ዕለት መጥታችሁ ስለጎበኛችሁን የላቀ ምስጋና እናቀርባለን ያሉት የባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራች ወ/ሮ ሀናን ሙሀመድ ለምታደርጉልን በርካታ የበጎ አድራጎት ስራ ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም አጠቃላይ በጎ አድራጎቱ ያለበትን ሁኔታ አስጎብኝተዋል ።
