አገልግሎቱ ወደ ERP የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት አሰራሩን ሲያዘምን ባለድርሻ አካላት ሚናቸዉ የላቀ መሆኑ ተገለፀ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት ከነበረዉ አሰራር ወደ ERP አሰራር ሲገባ ክፍተት እንዳይኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር በአገልግሎቱ አዳራሽ መጋቢት 12/2016 ዓ.ም ዉይይት የተደረገ ሲሆን በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ እንዳሉት ተቋሙ አሰራሩን በሚያዘምንበት ወቅት ባለድርሻ አካላት የግብዓት ቆጠራ ላይ የአቅም ግንባታና የግብዓት ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸዉ ጠቁመዋል።
አገልግሎቱ ከግሎባል ፈንድ ጋር ስለ ERP ትግበራ በቅርበት እየሰራ እንደሆና በቅርቡ ዋና መስሪያ ቤቱና 4 ቅርንጫፎች ዘመናዊዉን አሰራር የሚተገብሩ ሲሆን፤ በቀጣይ ቀሪዎቹ ቅርንጫፎች የቀድሞዉን ቪታስ ቴክኖሎጂ ሳያቋርጡ ወደ አዲሱ የERP ስርአት እንደሚሸጋገሩ የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አቅናዉ ካዉዛ ገልፀዋል።
ባለድርሻ አካላቱም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለዉን ስርአት ለመደገፍና ከግብአት ግዢ እስከ ስርጭት ድረስ ያለዉን አሰራር ለማዘመን የበኩላቸዉን ሀላፊነት እንደሚወጡ የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ተከታታይ የሆነ ምክክርና የድርጊት መርሀ-ግብር በመዉሰድ ሁሉም የበኩሉን ሚና የሚወጣ እንደሆነ በዉይይቱ የጋራ ተደርጓል።
# ማገልገል ክብር ነው!
ዘጋቢ ፦ አማኑኤል ወርቃየሁ
