አገልግሎቱ የቀጥታ የመድኃኒት ስርጭት አድማሱን በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ ከ Freight in Time Group (FIT) ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የቀጥታ የመድኃኒት ስርጭት አድማሱን በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ ከFIT ጋር ለአንድ አመት የሚቆይ ፕሮጀክት የመግባቢያ ሠነድ ስምምነት መጋቢት 5/2016 ዓ.ም ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ በላቸዉ እና የፕሮጀክቱ መሪ ወ/ሮ ዮዲት አድማሱ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት(USAID) ለአገልግሎቱ የመኪና ግዥ በማከናወን የቀጥታ ስርጭት አድማሱ እንዲስፋፋ ከማድረግ ጎን ለጎን በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆን ለFIT የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ከአገልግሎቱ ትዕዛዞችን ቶሎ ተቀብሎ ስርጭቱ የተሳለጠ እንዲሆን በማድረግ፤ የቁጥጥር ስራዎችን በመስራት፤ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት፤ የክትባትና የፕሮግራም ግብአቶች በፍጥነት እንዲደርሱ ለማድረግ የፕሮጀክቱ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ተናግረዋል፡፡
አገልግሎቱ 45% የክትባት እንዲሁም 60% የፕሮግራም ግብአቶችን ቀጥታ በማድረስ ቀሪዎች በወረዳ አና በዞን እያሰራጨ ሲሆን፤ ይህም ግብዓቶች በጊዜ አለመድረስ ለብልሽት እንደሚዳረጉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዉ ፤ በዚህም ግብአቶችን በ2 ወር ይደርስ የነበረዉን በ1ወር ዉስጥ በቀጥታ ተደራሽ ማድረግ የፕሮጀክቱ አላማ መሆኑን ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በዋናነት በአዲስ አበባ ቁጥር 1 እና 2፣ በጅማ እንዲሁም በባህርዳር ቅርንጫፎች ተግባራዊ በማድረግ ለ330 ጤና ተቋማት የክትባት አና የጤና ፕሮግራም ግብዓቶች በአንድ ላይ (Integret) በማድረግ በቀጥታ እንደሚያደርሱ ወ/ሮ ዮዲት ገልፀዋል፡፡
#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ
