አገልግሎቱ የተጠናቀቁ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን አስመረቀ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጷጉሜ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. የትውልድ ቀንን ምክንያት በማድረግ የህፃናት ማቆያ፣ የአስፋልት፣ ታሪካዊ ይዘቱን ሳይለቅ ያከናወነውን የቢሮ እድሳት፣ ለሰራተኞች ምቹ የስራ ከባቢ ለመፍጠር ያሰራውን የውሀ ፋውንቴን እና ካፍቴሪያ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወርቀሰሞ ማሞ መርቀው ከፍተዋል።
የተሰሩ መሰረተ ልማቶች በተለይ ለሰራተኛው ምቹ ከባቢን ለመፍጠር ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረው ይህን ላደረጉ ለአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እና የአገልግሎቱ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል።
በተያያዘ በግሎባል ፈንድ የበጀት ድጋፍ ተጀምሮ የነበረው የክትባት መድኃኒቶች ማቀዝቀዣ እና ተያያዥ አገልግሎቶች የሚሰጡበት ዘመናዊ ባለ 9 ወለል ህንፃ ከአለም ባንክ በተገኘ የበጀት ድጋፍ ይፋዊ የግንባታ ማጠናቀቂያ ስራ ክብርት ሚኒስትሯ አስጀምረዋል።
በመጨረሻም መሰረተ ልማቱ እንዲሰራ ላደረጉና ህንፃ ግንባታው የማጠናቀቂያ ስራ እንዲጀምር ላደረጉ አካላት አገልግሎቱ እውቅናና የምስክር ወረቀት አበርክቷል ።
#ማገልገል ክብር ነው
ሰላም ይደግ
